+ -

عَنْ سَهْلِ بْنِ مُعَاذِ بْنِ أَنَسٍ عَنْ أَبِيهِ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ أَكَلَ طَعَامًا فَقَالَ: الحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَطْعَمَنِي هَذَا وَرَزَقَنِيهِ مِنْ غَيْرِ حَوْلٍ مِنِّي وَلاَ قُوَّةٍ، غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ».

[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن الترمذي: 3458]
المزيــد ...

ሰህል ቢን ሙዓዝ ቢን አነስ ከአባቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ምግብ በልቶ ‹አልሐምዱ ሊላሂለዚ አጥዐመኒ ሀዛ ወረዘቀኒሂ ሚን ጘይሪ ሐውሊን ሚንኒ ወላቁውዋህ› ያለ ሰው ያሳለፈው ወንጀል ለርሱ ይማርለታል።"» ትርጉሙም "ያለኔ ኃይልና ብልሃት ይህንን ላበላኝና ለለገሰኝ አላህ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው።

[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3458]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምግብ የበላን ሰው አላህን እንዲያመሰግንና ምግብን በማምጣቱም በመብላቱም በአላህና በእገዛው ካልሆነ በቀር ለኔ ምንም አቅም የለኝም እንዲልም አነሳሱ። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን የተናገረ ሰው ላሳለፈው ትናንሽ ወንጀሎቹ የአላህን ምህረት ለማግኘት የተገባ እንደሆነ አበሰሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية النيبالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የምግብ መጨረሻ ላይ አላህን ማመስገን እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. አላህ ለባሮቹ ሲሳይን መለገሱን፣ የሲሳይን ምክንያት ለነርሱ ማግራቱንና በዚህም ወንጀላቸው መማሪያን ማድረጉን ስናይ የአላህን በባሮቹ ላይ ያለውን ትልቅ ትሩፋት መብራራቱን እንረዳለን።
  3. የባሮች ጉዳይ ባጠቃላይ ከአላህ ነው እንጂ በነርሱ ኃይልና ብልሃት አይደለም። የትኛውም ባሪያ ግን ሰበቦችን በመስራት የታዘዘ ነው።