1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ሐዲሥ በመሃላው የሙስሊምን ሐቅ ያለአግባብ የወሰደ ሰው አላህ ለርሱ እሳትን ግድ አድርጎበታል፤ ጀነትንም በርሱ ላይ እርም አድርጓል።" አንድ ሰውዬም ለርሳቸው እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የማለበት ጉዳይ) ትንሽም እንኳ ብትሆን (ይቀጣልን)?" እርሳቸውም "የአራክ እንጨት ቢሆን እንኳ! (ይቀጣበታል።)

عن أَبِي أُمَامَةَ إِياسِ بنِ ثَعْلَبَةَ الحَارِثِيِّ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنِ اقْتَطَعَ حَقَّ امْرِئٍ مُسْلِمٍ بِيَمِينِهِ، فَقَدْ أَوْجَبَ اللهُ لَهُ النَّارَ، وَحَرَّمَ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ» فَقَالَ لَهُ رَجُلٌ: وَإِنْ كَانَ شَيْئًا يَسِيرًا يَا رَسُولَ اللهِ؟ قَالَ: «وَإِنْ قَضِيبًا مِنْ أَرَاكٍ».

ከአቡ ኡማማህ ኢያስ ቢን ሠዕለበህ አልሓሪሢይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
«"በመሃላው የሙስሊምን ሐቅ ያለአግባብ የወሰደ ሰው አላህ ለርሱ እሳትን ግድ አድርጎበታል፤ ጀነትንም በርሱ ላይ እርም አድርጓል።" አንድ ሰውዬም ለርሳቸው እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የማለበት ጉዳይ) ትንሽም እንኳ ብትሆን (ይቀጣልን)?" እርሳቸውም "የአራክ እንጨት ቢሆን እንኳ! (ይቀጣበታል።)"»

ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 137

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሙስሊምን ሐቅ እያወቀ ያለአግባብ ለመውሰድ ዋሽቶ በአላህ ከመማል አስጠነቀቁ። የዚህ ተግባር ቅጣቱም እሳት መግባትና ጀነት መነፈግ ነው። ይህም ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው። አንድ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የተማለበት ነገር ትንሽ ብትሆን እንኳ?" አለ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "የወሰደው ለመፋቂያነት ከአራክ ዛፍ የሚወሰድ እንጨት እንኳ ብትሆን ይህን ቅጣት ይቀጣል።" አሉ።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. የሌሎችን ሐቅ መውሰድ መከልከሉን፤ ብታንስ እንኳ የሰዎችን ሐቅ ለባለቤቶቹ ለመስጠት መጣር እንደሚገባ፤ ዳኛ በስህተት የሚሰጠው ውሳኔ አንድ ሰው የራሱ ያልሆነን ሐቅ እንዲወስድ የተፈቀደ እንደማያደርግለት እንረዳለን።
  2. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "የሙስሊሞች ሐቅን ከባድነት እንረዳለን። እንዲሁም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "የአራክ እንጨት እንኳ ቢሆን!" ማለታቸው በትንሽና በትልቅ ሐቅ መካከልም (ከተጥያቂነት በኩል) ልዩነት እንደሌለው እንረዳለን።"
  3. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ቅጣት የሚመለከተው የሙስሊምን ሐቅ ያለአግባብ ወስዶ ከተውበት በፊት የሞተን ነው። ተውበት አድርጎ፣ በድርጊቱ ተፀፅቶ፣ ሐቁንም ወደ ባለቤቱ መልሶ ይቅርታውንም ጠይቆ፣ ወደመሰል ድርጊት ላይመለስም የቆረጠ ከሆነ ግን ወንጀለኝነቱ ከርሱ ላይ ተነስቶለታል።"
  4. ቃዲ እንዲህ ብለዋል: "ሐዲሡ ውስጥ የሙስሊም ሐቅ በማለት ተለይቶ የተጠቀሰው ሐዲሡ የሚመለከታቸው እነርሱ ስለሆኑና በሸሪዓ የሚተዳደሩት እነርሱ ስለሆኑ ነው እንጂ ከሙስሊም ውጪ የሆኑ ሰዎችን ሐቅ መውሰድ ይቻላል ማለት አይደለም። ይልቁንም ብይኑ እንደሙስሊሙ ብይን ነው።"
  5. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ውሸት ማለት አውቆም ሆነ ረስቶ፣ ስላለፈ ጉዳይም ሆነ ስለወደፊት አንድን ነገር ካለበት እውነታ ተቃራኒውን ማውራት ነው።"

ትርጉሞችን አሳይ

46 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
NE नेपाली النيبالية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية