عَنِ الحُسَينِ بنِ عَلِيٍّ بنِ أَبِي طَالِبٍ رضي الله عنهما قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«الْبَخِيلُ مَنْ ذُكِرْتُ عِنْدَهُ فَلَمْ يُصَلِّ عَلَيَّ».
[صحيح] - [رواه الترمذي والنسائي في الكبرى وأحمد] - [السنن الكبرى للنسائي: 8046]
المزيــد ...
ከሑሰይን ቢን ዐሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ተወስቼ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ነው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - - [አስሱነኑል ኩብራ ነሳኢ - 8046]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የርሳቸውን ስም ወይም ቅጥያ ስም ወይም ባህሪያቸውን በሚሰማ ወቅት እርሳቸው ላይ ሶላት ማውረድ የተወን ሰው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ: ስስታምነቱ የተሟላ ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ተወስቼ ሶለዋት ያላወረደብኝ ነው። ይህም የሆነው ከሚከተሉት ጉዳዮች አንፃር ነው:
የመጀመሪያው: ሶለዋት በማውረዱ ምክንያት ትንሽም ይሁን ብዙ የማይከስርበት፣ ገንዘብ የማያወጣበት፣ ጉልበቱን የማያፈስበት በሆነ ነገር ላይ መሰሰት ስለሆነ፤
ሁለተኛው: በአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶለዋት ባለማውረዱ በርሳቸው ላይ ሶላት የማውረድን ምንዳ በነፍሱ ላይ ስለሳሳና ስለነፈጋት ነው። በርሳቸው ላይ ሶለዋት ባለማውረዱ ትእዛዝን ለመተግበርና ምንዳን ለማግኘት ሊፈፅመው ግዴታ የሆነበትን ሐቅ ከመፈፀም ታቅቧልም ሰስቷልም።
ሶስተኛው: በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ የተወሰነውን የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሐቅ መወጣት ነው። ያስተማሩን፣ ያቀኑን፣ ወደ አላህ ተባረከ ወተዓላ የጠሩን፣ ይህንን ወሕይና ሸሪዓ ይዘው የመጡልን እርሳቸው ናቸው። ከአላህ ተባረከ ወተዓላ በኋላ የመመራታችን ምክንያት እርሳቸው ናቸው። በርሳቸው ላይ ሶለዋት ያላወረደ ሰው በርግጥም በነፍሱ ላይም ስስታም ሆኗል። ለነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ካላቸው ሐቆች መካከል በትንሹ ሐቅ እንኳ ስስታም ሆኗል።