ንዑስ ምድቦች

የሓዲሦች ዝርዝር

በአንድ ስፍራ ላይ አርፎ ከዚያም ‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ አትታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ (ምሉዕ በሆኑ የአላህ ቃላት ከፈጠራቸው ጎጂ ነገሮች እጠበቃለሁ)› ያለ ሰው ከዛ ስፍራ እስኪንቀሳቀስ ድረስ አንዳችም አይጎዳውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እኔ አንዲት ንግግር አውቃለሁ። እርሷን ቢናገራት አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል። አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧን ቢል አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ተወስቼ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ምግብ በልቶ ‹አልሐምዱ ሊላሂለዚ አጥዐመኒ ሀዛ ወረዘቀኒሂ ሚን ጘይሪ ሐውሊን ሚንኒ ወላቁውዋህ› ያለ ሰው ያሳለፈው ወንጀል ለርሱ ይማርለታል።"» ትርጉሙም "ያለኔ ኃይልና ብልሃት ይህንን ላበላኝና ለለገሰኝ አላህ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከጠየቃችሁት የተሻለን ነገር አልጠቁማችሁምን? መኝታ ስፍራችሁን የያዛችሁ ጊዜ ወይም ወደ መኝታችሁ ስፍራ የተጠጋችሁ ጊዜ ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'ሱብሓነላህ' ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'አልሐምዱሊላህ' ሰላሳ አራት ጊዜ ደግሞ 'አላሁ አክበር' በሉ። ይህም ለናንተ ከአገልጋይ የተሻለ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ንፋስን አትሳደቡ! የምትጠሉትን ነገር በተመለከታችሁ ጊዜ "አላህ ሆይ! ከዚህች ንፋስ መልካሙን፣ በውስጧ የያዘችውንም መልካም ነገር፣ የታዘዘችውንም መልካም ነገር እንጠይቅሃለን፤ ከዚህች ንፋስ ጉዳት፣ ውስጧ ከያዘችው ጎጂ ነገር፣ ከታዘዘችውም መጥፎ ነገር በአንተ እንጠበቃለን።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እርሱ ዘንድ ስሜ ተወስቶ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ረመዷንን አግኝቶ ከዚያም ከመማሩ በፊት የወጣበት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ወላጆቹን እርጅና ላይ አግኝቶ ጀነት ያላስገቡት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ