عن خَوْلَةَ بِنْتَ حَكِيمٍ السُّلَمِيَّةَ قَالتْ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«مَنْ نَزَلَ مَنْزِلًا ثُمَّ قَالَ: أَعُوذُ بِكَلِمَاتِ اللهِ التَّامَّاتِ مِنْ شَرِّ مَا خَلَقَ، لَمْ يَضُرَّهُ شَيْءٌ حَتَّى يَرْتَحِلَ مِنْ مَنْزِلِهِ ذَلِكَ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2708]
المزيــد ...
ከኸውለህ ቢንት ሐኪም አስሱለሚየህ እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
"በአንድ ስፍራ ላይ አርፎ ከዚያም ‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ አትታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ (ምሉዕ በሆኑ የአላህ ቃላት ከፈጠራቸው ጎጂ ነገሮች እጠበቃለሁ)› ያለ ሰው ከዛ ስፍራ እስኪንቀሳቀስ ድረስ አንዳችም አይጎዳውም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2708]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰው ልጅ አንድ ስፍራ ላይ በሚያርፍበት ጊዜ የሚፈራቸውን ሁሉ አስፈሪ ነገሮች የሚከላከልበትን ጠቃሚ መጠበቂያና መጠጊያ ለኡመታቸው እየጠቆሙ ነው። ይህም ጉዞም ላይ ይሁን ሊዝናናም ይሁን ወይም ከዛ ውጪ ባረፈበት ስፍራ ላይ ከሚገኝ ፍጡራን ሁሉ ክፋት በትሩፋቱ፣ በበረከቱና በጥቅሙ የተሟላ በሆነውና ከሁሉም ነውርና ጉድለት የፀዳ በሆነው የአላህ ቃል ከተጠበቀና ከተጠጋ በዛ ስፍራ እስካለ ድረስ ከሁሉም ጎጂ ነገሮች ደህንነቱ ይጠበቃል።