عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤمنينَ رضي الله عنها قَالَتْ:
دَخَلَ عَلَيَّ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، وَقَدْ سَتَرْتُ سَهْوَةً لِي بِقِرَامٍ فِيهِ تَمَاثِيلُ، فَلَمَّا رَآهُ هَتَكَهُ وَتَلَوَّنَ وَجْهُهُ وَقَالَ: «يَا عَائِشَةُ، أَشَدُّ النَّاسِ عَذَابًا عِنْدَ اللهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ الَّذِينَ يُضَاهُونَ بِخَلْقِ اللهِ» قَالَتْ عَائِشَةُ: «فَقَطَعْنَاهُ فَجَعَلْنَا مِنْهُ وِسَادَةً أَوْ وِسَادَتَيْنِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2107]
المزيــد ...
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
"እቃ ክፍሌን (የተንቀሳቃሽ እንስሳ) ምስል ባለበት መጋረጃ ሸፍኜው ሳለ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኔ ዘንድ መጡ። የተመለከቱት ጊዜም ፊታቸው ተለዋውጦ ቀደዱትና እንዲህም አሉ 'ዓኢሻ ሆይ! የትንሳኤ ቀን አላህ ዘንድ ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ ቅጣት የሚቀጡት እነዚያ በአላህ ፍጥረት የሚፎካከሩት ናቸው።'" ዓኢሻም እንዲህ አለች "ቆርጠነው በርሱ አንድ ትራስ ወይም ሁለት ትራስ አደረግንበት።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2107]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤታቸው ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድ ሲገቡ እቃ የምታስቀምጥበትን ትንሽዬ ክፍል ነፍስ ያላቸው ምስሎች ባለበት መጋረጃ ሸፍናው አገኟት። የፊታቸው ቀለምም ለአላህ ብለው በመቆጣታቸው ምክንያት ተለዋውጦ መጋረጃውን አወለቁት። እንዲህም አሉ: የትንሳኤ ቀን ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ ቅጣት የሚቀጡት የአላህን ፍጥረት አስመስለው ምስል የሚያደርጉት ናቸው። ዓኢሻም እንዲህ አለች: እርሱን አንድ ትራስ ወይም ሁለት ትራስ አደረግነው።