عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما:
أَنَّ رَجُلًا أَتَى النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَكَلَّمَهُ فِي بَعْضِ الْأَمْرِ، فَقَالَ: مَا شَاءَ اللهُ وَشِئْتَ، فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «أَجَعَلْتَنِي لِلَّهِ عَدْلًا؟ قُلْ: مَا شَاءَ اللهُ وَحْدَهُ».
[إسناده حسن] - [رواه ابن ماجه والنسائي في الكبرى وأحمد] - [السنن الكبرى للنسائي: 10759]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
"አንድ ሰውዬ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣና በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ አውርቷቸው 'የአላህና የእርሶ መሻት ሆነ።' አለ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ለአላህ ቢጤ አደረግከኝን? የብቸኛው አላህ መሻት ሆነ! በል!' አሉት።"
[ሰነዱ ሐሰን ነው።] - [ኢብኑ ማጀህ፣ ነሳኢ በኩብራ ውስጥ፣ አሕመድ ዘግበውታል።] - [አስሱነኑል ኩብራ ነሳኢ - 10759]
አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት የግሉን ጉዳይ አወራቸውና ከዚያም "የአላህና የእርሶ መሻት ሆነ።" አላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህ ንግግሩን አወገዙት። የፍጡርን መሻት ከአላህ መሻት ጋር አቆራኝቶ መናገር ሙስሊም ሊለው የማይፈቀድለት ትንሹ ሺርክ መሆኑን ተናገሩ። ቀጥለውም ትክክለኛው አባባል "የብቸኛው አላህ መሻት ሆነ።" ማለቱ እንደሆነ ጠቆሙት። አላህን በመሻቱ መነጠል እንጂ በማንኛውም ማቆራኛ ቃላት የአንድንም አካል መሻት ከአሏህ ጋር ማቆራኘት የለበትም።