+ -

عَنْ أَبِي وَاقِدٍ اللَّيْثِيِّ رضي الله عنه:
أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لَمَّا خَرَجَ إِلَى حُنَيْنٍ مَرَّ بِشَجَرَةٍ لِلْمُشْرِكِينَ يُقَالُ لَهَا: ذَاتُ أَنْوَاطٍ يُعَلِّقُونَ عَلَيْهَا أَسْلِحَتَهُمْ، فَقَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، اجْعَلْ لَنَا ذَاتَ أَنْوَاطٍ كَمَا لَهُمْ ذَاتُ أَنْوَاطٍ، فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «سُبْحَانَ اللهِ! هَذَا كَمَا قَالَ قَوْمُ مُوسَى {اجْعَلْ لَنَا إِلَهًا كَمَا لَهُمْ آلِهَةٌ} [الأعراف: 138] وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ لَتَرْكَبُنَّ سُنَّةَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ».

[صحيح] - [رواه الترمذي وأحمد]
المزيــد ...

ከአቡ ዋቂድ አል-ለይሢይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፉት:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ሑነይን የወጡ ጊዜ 'ዛቱ አንዋጥ' በምትባል የአጋርያን ዛፍ በኩል አለፉ። በርሷ ላይ (በረከትን በመፈለግ) መሳሪያዎቻቸውን ያንጠለጥሉባት ነበር። ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለነርሱ ‹ዛቱ አንዋጥ› እንዳላቸው ለኛም (የምናንጠለጥልበት) ‹ዛቱ አንዋጥ› አድርግልን።' አሉ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ 'ለአላህ ጥራት ተገባው! ይህ (የተናገራቹት) የሙሳ ህዝቦች {ለእነርሱ አማልክት እንዳላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን።} [አል አዕራፍ: 138] ብለው እንደተናገሩት ነው። ያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዬ እምላለሁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች መንገድ ትከተላላችሁ።'"

ሶሒሕ ነው። - ቲርሚዚ ዘግበውታል።

ትንታኔ

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ሑነይን ወጡ። ሑነይን: በጧኢፍና መካ መካከል የሚገኝ ሸለቆ ነው። ከርሳቸውም ጋር የሚጓዙ በቅርብ ወደ ኢስላም የገቡ የተወሰኑ ሶሐቦች ነበሩ። "ዛቱ አንዋጥ" ማለትም የመንጠልጠያ ባለቤት በምትባል ዛፍ በኩል አለፉ። ዛፊቱ አጋርያን ያልቋትና መሳሪያዎቻቸውንና ሌሎች ነገሮችንም በረከትን በመፈለግ የሚያንጠለጥሉባት ዛፍ ነበረች። ከመልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነርሱ በረከትን ለመፈለግ መሳሪያዎቻቸውን የሚያንጠለጥሉበት የርሷ አምሳያ ዛፍ እንዲያደርጉላቸው ፈለጉ። ይህም የሚፈቀድ ነገር ስለመሰላቸው ነው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን ንግግራቸው እያወገዙ አላህን በማላቅ ተስቢሕ አደረጉ። ይህ ንግግር የሙሳ ህዝቦች {ለእነርሱ አማልክት እንዳላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን።} በማለት ለሙሳ የተናገሩትን ንግግር እንደሚመስልም ተናገሩ። የሙሳ ህዝቦች ጣኦት የሚያመልክን በተመለከቱ ጊዜ አጋርያን ጣኦት እንዳላቸው ለነርሱም ጣኦት እንዲኖራቸው ፈለጉ። ይህ ግን የነርሱን መንገድ መከተል ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህ ህዝብ የየሁዶችንና የክርስቲያኖችን መንገድ እንደሚከተልና የነርሱን ድርጊት እንደሚፈፅም በማስጠንቀቅ መልኩ ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الغوجاراتية القيرقيزية النيبالية اليوروبا الدرية الصومالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሰው ልጅ አንዳንዴ አንዳች ነገር ከአሏህ የሚያርቀው ሆኖ ሳለ ወደ አላህ የሚያቃርበው እንደሆነ አድርጎ ሊያስበው ይችላል።
  2. አንድ ሙስሊም በሃይማኖት በኩል ሊባል የማይገባን ነገር የሰማ ጊዜና የተደነቀ ጊዜ ተስቢሕና ተክቢር ማድረግ ይገባዋል።
  3. ከሺርክ መካከል በዛፍ፣ በድንጋይና በሌሎች ነገሮች በረከት መፈለግ አንዱ ነው። በረከት የምንፈለገው ከአላህ ብቻ ነው።
  4. የጣኦት አምልኮ መንስኤው ጣኦትን ማላቅ፣ እርሱ ዘንድ አዘውትሮ መቀመጥና በርሱ በረከትን መፈለግ ነው።
  5. ወደ ሺርክ የሚያዳርሱ መንገዶችንና በሮችን መዝጋት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  6. በቁርአንና ሐዲሥ ውስጥ አይሁድና ክርስትያኖችን በማውገዝ የመጡ ጥቅሶች ለኛ ማስጠንቀቂያ ናቸው።
  7. የኛ እምነት አካል መሆኑን የሚጠቁም ማስረጃ እስካልመጣ ድረስ ከድንቁርና ዘመን ሰዎች፣ ከየሁዶችና ከክርስቲያኖች ጋር መመሳሰል መከልከሉን እንረዳለን።