+ -

عَنْ عَلِيٍّ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ لِي رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«قُلِ اللهُمَّ اهْدِنِي وَسَدِّدْنِي، وَاذْكُرْ بِالْهُدَى هِدَايَتَكَ الطَّرِيقَ، وَالسَّدَادِ سَدَادَ السَّهْمِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2725]
المزيــد ...

ከዓሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉኝ:
"'አሏሁመ‐ህዲኒ ወሰዲድኒ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ ምራኝ፣ አስተካክለኝም።) በልና መመራትን ከአሏህ ስትጠይቅ መንገድን መመራትን አስታውስ። መስተካከልን ስትጠይቅ ደሞ የቀስት ኢላማውን የማግኘት ያህል መገጠምን አስታውስ።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2725]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዓሊይ ቢን አቢ ጣሊብን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አላህን እንዲህ ብሎ እንዲጠይቅና እንዲለምን አዘዙት "አላህ ሆይ! ምራኝ" አቅናኝ፣ ጠቁመኝ "አስተካክለኝ" ግጠመኝ፣ በሁሉም ጉዳዮቼ የተቃና አድርገኝ።
ሁዳ (መመራት) ማለት እውነትን በዝርዝርም ሆነ በጥቅሉ ማወቅና እውነትን በግልፅም ሆነ በውስጥ ለመከተል መገጠም ማለት ነው።
ሰዳድ "መስተካከል" ማለት: በሁሉም ነገሮች በእውነት ላይ ትክክል በሚሆነው ቀጥ ማለትና መገጠም ማለት ነው። "ሰዳድ" ማለት በንግግርም፣ በተግባርም ሆነ በእምነት ቀጥተኛ የሆነ መንገድ ማለት ነው።
ሀሳባዊ ነገር በህዋሳዊ ነገሮች ይብራራሉና አንተ ይህን ዱዓ እያደረግክ "መመራትን ስትማፀን የመንገድ መመራትን" አስታውስ፤ ጉዞ የወጣ ሰው መንገድ መመራት እንደሚጠይቀው መመራት እየጠየቅክ እንደሆነ ቀልብህ ላይ አስቀምጥ። መንገድ የወጣ ሰው ከተመራው መንገድ ከመጥፋት ለመዳን ወደቀኝ ወይም ወደግራ ዘንበል አይልም። ቀጥ ብሎ በመሄዱም ሰላምን ያገኛልም ወደ አላማውም በፍጥነት ይደርሳል።
"መስተካከልን ስትጠይቅ ደሞ ቀስት ኢላማውን የማግኘትን ያህል መገጠምን አስታውስ።" አንተ ቀስት ስታነጣጥር በፍጥነት መድረሱንና ኢላማውን ማግኘቱ ላይ ነው የምታተኩረው። ቀስት ወርዋሪ ወደ አንድ ኢላማ ባነጣጠረ ወቅት ቀስቱን ወደ ኢላማው አስተካክሎ ያነጣጥራል። ልክ እንደዚሁ ያሰብከውን መገጠም እንደቀስቱ የተስተካከለ እንዲሆን አድርገህ ነው አላህን የምትጠይቀው። በጥያቄህም የፈለግከው የመመራትን ጥግና የመገጠምን ድካ ይሆናል ማለት ነው።
በዚህ ዱዓ ስትማፀን የምትፈልገውን ጉዳይ ቀስት ስትወረውር እንደምታልመው ትክክለኝነት እንዲሆን አላህን መገጠም ስትጠይቅ በቀልብህ ይህን ሀሳብ አስቀምጥ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ዱዓ አድራጊ ስራው እንዲስተካከልና እንዲቃና ሱናን በማጥበቅና ኒያን በማጥራት ላይ ሊጥር ይገባዋል።
  2. ለመገጠምና ለመስተካከል በነዚህ ጠቅላይ ቃላቶች ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  3. አንድ ባሪያ ለሁሉም ጉዳዮቹ በአላህ መታገዝ ይገባዋል።
  4. በማስተማር ወቅት ምሳሌ ማድረግ እንደሚገባ እንረዳለን።
  5. መመራትን፣ የሁኔታዎች መስተካከልን እና የአይን ርግብግቢት ያህል እንኳ ከርሱ ሳይጣመሙ መጨረሻ በማስተካከል በርሱ ላይ መዘውተርን አንድ ላይ ሰብስበው ዱዓእ ማድረጋቸውን እንረዳለን። "ምራኝ" የሚለው ቃል በመመራት ጎዳና ላይ የሚጓዝ መሆንን መጠየቅ ነው። "አስተካክለኝ" የሚለው ቃል ደግሞ ኢላማን ማግኘት፣ በመመራት ወቅት አለመጥመምን የሚጠቁም ነው።
  6. ዱዓ አድራጊ በዱዓው ትኩረት ሊሰጥ፣ የዱዓውንም ትርጉም ወደ ቀልቡ ማቅረብ ይገባዋል። ይህም ዱዓው ተቀባይነት እንዲያገኝ ይረዳዋል።