عن أنس بن مالك رضي الله عنه:
أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَمُعَاذٌ رَدِيفُهُ عَلَى الرَّحْلِ قَالَ: «يَا مُعَاذُ بْنَ جَبَلٍ»، قَالَ: لَبَّيْكَ يَا رَسُولَ اللهِ وَسَعْدَيْكَ، قَالَ: «يَا مُعَاذُ»، قَالَ: لَبَّيْكَ يَا رَسُولَ اللهِ وَسَعْدَيْكَ، ثَلَاثًا، قَالَ: «مَا مِنْ أَحَدٍ يَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ صِدْقًا مِنْ قَلْبِهِ إِلَّا حَرَّمَهُ اللهُ عَلَى النَّارِ»، قَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ، أَفَلَا أُخْبِرُ بِهِ النَّاسَ فَيَسْتَبْشِرُوا؟ قَالَ: «إِذًا يَتَّكِلُوا». وَأَخْبَرَ بِهَا مُعَاذٌ عِنْدَ مَوْتِهِ تَأَثُّمًا.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 128]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው:
"ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ግመል ላይ ሆነው ሙዓዝ ከኃላ ተፈናጦ ሳለ እንዲህ አሉ: 'አንተ ሙዓዝ ቢን ጀበል ሆይ' እርሱም ሶስቴ 'አቤት ብያለው በደስታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!' አሁንም 'ሙዓዝ ሆይ!' አሉት: እሱም 'አቤት ብያለው በደስታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!' አለ። ሶስት ጊዜ ደገሙትና ቀጥለውም ' አላህ በእርሱ ላይ እሳትን እርም ቢያደርግ እንጂ አንድም በእውነተኛ ልቡ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን የሚመሰክር የለም።' አሉ። እርሱም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህንን ለሰዎች ነገሬ ላበስራቸው እንዴ?' አለ። እሳቸውም 'ከነገርካቸውማ (በዚህ ሐዲሥ ላይ) ይደገፋሉ (ይሰንፋሉ)።' አሉ። ሙዓዝ ይህንን ሐዲስ የተናገረው ወንጀል ውስጥ ላለ መውደቅ ብሎ ሊሞት ሲል ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 128]
ሙዓዝ ቢን ጀበል -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መጋጓዣ ኋላ ተፈናጦ ሳለ እሳቸው "ሙዓዝ ሆይ!" በማለት ጠሩት። ለርሱ የሚነግሩት ነገር አንገብጋቢ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠትም ጥሪያቸውን ሶስት ጊዜ ደጋገሙት።
ሙዓዝም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- በነዚህ ጥሪዎች ሁሉ "ለበይከ ያረሱለሏህ ወሰዕደይክ" ማለትም የአላህ መልክተኛ ሆይ!ደጋግሜ በደስታ አቤት ብያለሁ። እያለ ይመልስ ነበር።
ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ሳይዋሽ በእውነተኛ ልቡ የሚመሰክር ሆኖ በዚህ ሁኔታው ላይ ከሞተ አላህ እሳትን በርሱ ላይ እርም እንደሚያደርግ ነገሩት።
ሙዓዝም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ሰዎች እንዲደሰቱና በመልካም እንዲበሰሩ ልንገራቸውን? በማለት ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠየቀ።
ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዚህች ንግግር ላይ በመደገፍ ስራዎቻቸው እንዳታንስ ፈሩ።
ሙዓዝም እውቀትን የመሸሸግ ወንጀል ውስጥ መውደቅን በመፍራት ከመሞታቸው በፊት ካልሆነ በቀር ከዛ በፊት ይህችን ሐዲሥ ለአንድም አልተናገረም።