عَنْ عُمَرَ بْنِ الخَطَّابِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ:
قَدِمَ عَلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ سَبْيٌ، فَإِذَا امْرَأَةٌ مِنَ السَّبْيِ قَدْ تَحْلُبُ ثَدْيَهَا تَسْقِي، إِذَا وَجَدَتْ صَبِيًّا فِي السَّبْيِ أَخَذَتْهُ، فَأَلْصَقَتْهُ بِبَطْنِهَا وَأَرْضَعَتْهُ، فَقَالَ لَنَا النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «أَتُرَوْنَ هَذِهِ طَارِحَةً وَلَدَهَا فِي النَّارِ؟» قُلْنَا: لاَ، وَهِيَ تَقْدِرُ عَلَى أَلَّا تَطْرَحَهُ، فَقَالَ: «لَلَّهُ أَرْحَمُ بِعِبَادِهِ مِنْ هَذِهِ بِوَلَدِهَا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5999]
المزيــد ...
ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
«ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ምርኮኞች ገቡ። ድንገት ከምርኮኞቹ መካከል አንድ ሴት ጡቶቿን እያለበች ልጅን የምታጠባ ነበረች። ከምርኮኞች መካከል ልጇን ስታገኝ ያዘችውና ወደ ሆዷ አስጠግታ ጡቷን አጠባችው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለኛ እንዲህ አሉን: "ይህቺ ሴትዮ ልጇን እሳት ውስጥ ትጥላለች ብላችሁ ታስባላችሁን?" እኛም "አለመጣል እስከቻለች ድረስ በፍፁም አትጥለውም።" አልን። እርሳቸውም "ይህቺ ለልጇ ካላት እዝነት የበለጠ አላህ ለባሮቹ ያዝንላቸዋል።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5999]
ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የሃዋዚን ምርኮኞች መጡላቸው። ድንገት ከነርሱ መካከል አንዲት ሴት ልጇን ትፈልግ ጀመር። አንድ ህፃን ስታገኝም ወተት በጡቷ ውስጥ በመጠራቀሙ ስለተጎዳች ትይዘውና ታጠባዋለች። ከምርኮኞች መካከልም ልጇን አግኝታ ያዘችውና ወደ ሆዷ አቅፋ ደግፋ አጠባችው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለባልደረቦቻቸው እንዲህ አሉ: "ይህቺ ሴትዮ ልጇን እሳት ውስጥ ትጥላለች ብላችሁ ታስባላችሁን?" እኛም "በራሷ ፍቃድ ማንም ሳያስገድዳት መቼም አትጥለውም።" አልናቸው። እርሳቸውም "አላህ ለሙስሊም ባሮቹ ይህቺ ለልጇ ካላት እዝነት የበለጠ እጅግ አዛኝ ነው።" አሉ።