عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ وَعَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنهما عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ:
«مَا يُصِيبُ الْمُسْلِمَ مِنْ نَصَبٍ وَلَا وَصَبٍ وَلَا هَمٍّ وَلَا حُزْنٍ وَلَا أَذًى وَلَا غَمٍّ حَتَّى الشَّوْكَةِ يُشَاكُهَا إِلَّا كَفَّرَ اللهُ بِهَا مِنْ خَطَايَاهُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5641]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይና አቡ ሁረይራህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"አንድን ሙስሊም ድካም፣ በሽታ፣ ሀሳብ፣ ሀዘን፣ ጉዳት፣ ጭንቀት የምትወጋው አንዲት እሾክ እንኳ (በከንቱ) አታገኘውም አላህ በሷ ምክንያት ከወንጀሎቹ የሚምርለት ቢሆን እንጂ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5641]
ሙስሊምን ከበሽታዎች ፣ ከጭንቀቶች፣ ከሀዘኖች፣ ከችግሮች፣ ከመከራዎች፣ ከመአቶች እንዲሁም ከፍርሀትና ረሀብ ቢደርስበት አንዲት እሾህ እንኳ ብትወጋውና ብታሳምመው ለርሱ ወንጀሎቹን ማስማሪያና ኃጢአቶቹን ማስሰረያ እንደሚሆንለት የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።