+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«رَغِمَ أَنْفُ رَجُلٍ ذُكِرْتُ عِنْدَهُ فَلَمْ يُصَلِّ عَلَيَّ، وَرَغِمَ أَنْفُ رَجُلٍ دَخَلَ عَلَيْهِ رَمَضَانُ ثُمَّ انْسَلَخَ قَبْلَ أَنْ يُغْفَرَ لَهُ، وَرَغِمَ أَنْفُ رَجُلٍ أَدْرَكَ عِنْدَهُ أَبَوَاهُ الكِبَرَ فَلَمْ يُدْخِلاَهُ الجَنَّةَ».

[صحيح] - [رواه الترمذي وأحمد] - [سنن الترمذي: 3545]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"እርሱ ዘንድ ስሜ ተወስቶ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ረመዷንን አግኝቶ ከዚያም ከመማሩ በፊት የወጣበት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ወላጆቹን እርጅና ላይ አግኝቶ ጀነት ያላስገቡት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3545]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶስት አይነት ሰዎችን በውርደትና ክስረት አፍንጫቸው በአፈር እንዲታሽ ረገሟቸው: የመጀመሪያው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እርሱ ዘንድ ተወስተው በርሳቸው ላይ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወይም እርሱን የመሰለ ውዳሴ በማለት በርሳቸው ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው ነው። ሁለተኛው: የረመዷንን ወር አግኝቶ ከዚያም አምልኮን በአግባቡ ባለመፈፀሙ ምክንያት ከመማሩ በፊት ወሩ የተጠናቀቀበት ሰው ነው። ሶስተኛው: በእርጅና ወቅት ወላጆቹን አግኝቶ የነርሱን ሐቅ ባለመወጣቱና ሐቃቸውን በማጓደሉ ምክንያት ጀነት ለመግባቱ ሰበብ ያልሆኑለት ሰው ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "ዋናው ፍሬ ሃሳብ እያንዳንዱ እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱት አካላት እድሉን ቢጠቀምበት ኖሮ ትልቅ መልካም የሆነን እድል የሚያገኝበት ነገር ነበረው። እድሉን በሚያመልጠው ልክ ማጓደሉ ግን ለክስረትና ለውርደት ዳረገው።"
  2. የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስም በተወሳ ቁጥር በርሳቸው ላይ ሶላት በማውረድ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  3. በረመዷን ወር ለአምልኮ በመዘጋጀትና በመታገል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  4. ለወላጆች በጎ በማድረግና በመንከባከብ መታገል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። በተለይ ባረጁ ወቅት የበለጠ መታገል ተገቢ ነው።