عَنْ أُبَيِّ بْنِ كَعْبٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لاَ تَسُبُّوا الرِّيحَ، فَإِذَا رَأَيْتُمْ مَا تَكْرَهُونَ فَقُولُوا: اللَّهُمَّ إِنَّا نَسْأَلُكَ مِنْ خَيْرِ هَذِهِ الرِّيحِ وَخَيْرِ مَا فِيهَا وَخَيْرِ مَا أُمِرَتْ بِهِ، وَنَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ هَذِهِ الرِّيحِ وَشَرِّ مَا فِيهَا وَشَرِّ مَا أُمِرَتْ بِهِ».
[صحيح] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 2252]
المزيــد ...
ኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
"ንፋስን አትሳደቡ! የምትጠሉትን ነገር በተመለከታችሁ ጊዜ "አላህ ሆይ! ከዚህች ንፋስ መልካሙን፣ በውስጧ የያዘችውንም መልካም ነገር፣ የታዘዘችውንም መልካም ነገር እንጠይቅሃለን፤ ከዚህች ንፋስ ጉዳት፣ ውስጧ ከያዘችው ጎጂ ነገር፣ ከታዘዘችውም መጥፎ ነገር በአንተ እንጠበቃለን።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2252]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ንፋስን ከመሳደብና ከመርገም ከለከሉ። ምክንያቱም ንፋስ ከፈጣሪዋ የታዘዘች በመሆኗ እዝነትና ቅጣትን ይዛ ትመጣለች። እርሷን መስደብ ፈጣሪዋን አላህን መሳደብና በውሳኔው ማማረር ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከንፋሷ መልካም ነገር፣ ውስጧ ከያዘችው መልካም ነገርና ዝናብ ይዞ እንደመምጣት፣ ዘርን እንደማራባትና በመሳሰሉት የተላከችበትን መልካም ነገር አላህን በመጠየቅና ከንፋሷ ጉዳት፣ ውስጧ ከያዘችው ጉዳት፣ ቡቃያንና ዛፍን እንደ ማጥፋት፣ እንስሶችን ማጥፋት፣ ህንፃዎችን እንደማፍረስና ከመሳሰሉት ከተላከችበት ጎጂ ነገር በአላህ በመጠበቅ ወደ አላህ እንድንመለስ ጠቆሙ። አላህን ይህን መጠየቅ አምልኮን ለአላህ ማረጋገጣችንን ይጠቁማል።