عن أنس رضي الله عنه قال: قال النبي صلى الله عليه وسلم:
«لَا يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى أَكُونَ أَحَبَّ إِلَيْهِ مِنْ وَالِدِهِ وَوَلَدِهِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከአነስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ ከወላጆቹ ፣ ከልጁና ከሰዎች ባጠቃላይ እርሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ እኔ እስክሆን ድረስ አላመነም።'"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari]

ትንታኔ

አንድ ሙስሊም ለአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያለው ውዴታ ለእናቱ ፣ ለአባቱ ፣ ለወንድ ልጁ፣ ለሴት ልጁና ለሰዎችም ባጠቃላይ ካለው ውዴታ እስኪያስቀድም ድረስ ኢማኑ ምሉዕ አይሆንም በማለት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። ይህ ውዴታም እሳቸውን መታዘዝን፣ መርዳትንና እሳቸውን ማመፅ መተውን ያስፈርዳል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. መልክተኛውን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መውደድና ከሁሉም ፍጡራን ውዴታ ማስቀደም ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  2. የአላህን መልክተኛ ሱና መርዳትና በዚህ መንገድ ላይም ገንዘብና ነፍስን መለገስ ከተሟላ ውዴታ ምልክቶች መካከል አንዱ ነው።
  3. መልክተኛውን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መውደድ ባዘዙት ነገር መታዘዝን ፣ በተናገሩት ማመንን፣ ከከለከሉትና ካስጠነቀቁት ነገሮች መከልከልን፣ እሳቸውን መከተልንና ቢድዓን መተው ያስፈርዳል።
  4. ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጥመት መንገድ (ወደ ቀናው) ለመመራታችን ፣ ከእሳት ለመዳናችን፣ ጀነትን ለመጎናፀፋችን ምክንያት ስለሆኑ የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሀቅ ከሁሉም ሰዎች ሀቅ የበለጠና የገዘፈ ነው።