عَنْ سَلْمَانَ الْفَارِسِيِّ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«ثَلَاثَةٌ لَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ: أُشَيْمِطٌ زَانٍ، وَعَائِلٌ مُسْتَكْبِرٌ، وَرَجُلٌ جَعَلَ اللَّهَ لَهُ بِضَاعَةً، فَلَا يَبِيعُ إِلَّا بِيَمِينِهِ وَلَا يَشْتَرِي إِلَّا بِيَمِينِهِ».
[صحيح] - [رواه الطبراني] - [المعجم الصغير: 821]
المزيــد ...
ከሰልማን አልፋሪሲይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ሶስት አይነት ሰዎች አላህ የትንሳኤ ቀን አያናግራቸውም። ከወንጀላቸውም አያጠራቸውም። ለነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው። የሽማግሌ ዝሙተኛ፣ የድሃ ኩራተኛና አላህን ሸቀጡ ያደረገ ሰው ነው። ያለመሃላ አይሸጥም። ያለመሃላው አይገዛም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [At-Tabaraani]
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የትንሳኤ ቀን ተውበት እስካላደረጉ ወይም አላህ ቅጣቱን ይቅር እስካላላቸው ድረስ ቅጣት ስለሚገባቸው ሶስት የሰዎች አይነት ተናገሩ። የመጀመሪያው ቅጣት: የትንሳኤ ቀን አላህ በጣም ስለሚቆጣባቸው አያናግራቸውም። ይልቁንም እነርሱን ችላ ይላል። ወይም በነርሱ ላይ መቆጣቱን የሚጠቁም የማያስደስታቸውን ንግግር ያናግራቸዋል። ሁለተኛው ቅጣት: አያጠራቸውም፣ በነርሱ ላይ አያወድስም፣ ከወንጀላቸውም አያጠራቸውም። ሶስተኛው ቅጣት: በመጪው አለም አሳማሚና ብርቱ ቅጣት አላቸው። እነዚህም ሰዎች: የመጀመሪያው: ዝሙት ላይ የሚወድቅ ያረጀ ሰውዬ ነው። ሁለተኛው: ገንዘብ የሌለው ድሃ ከመሆኑም ጋር ሰዎች ላይ ይኮራል። ሶስተኛው: ሲሸጥና ሲገዛ በአላህ መማል የሚያበዛ ሰው ነው። በዚህም የአላህን ስም ዝቅ ያደርጋል። የአላህን ስምም ገንዘብ ማግኛ ያደርገዋል።