عن سالم بن أبي الجَعْدِ قال: قال رجل: ليتني صَلَّيتُ فاسترحْتُ، فكأنّهم عابُوا ذلك عليه، فقال: سمعتُ رسولَ الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«يا بلالُ، أقِمِ الصَّلاةَ، أرِحْنا بها».
[صحيح] - [رواه أبو داود] - [سنن أبي داود: 4985]
المزيــد ...
ከሳሊም ቢን አቢ ጀዕድ እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: "አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: 'ምናለ ሰግጄ እረፍት ባገኘሁ።' አለ። ሰዎቹ በዚህ ንግግሩ ላይ ያነወሩት መስሎ ሲታይም እንዲህ አለ: 'የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
‹ቢላል ሆይ! ሶላትን ኢቃም ብለህ በሶላት እረፍት ስጠን።›'"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4985]
ከሶሐቦች መካከል አንዱ "ምናለ ሰግጄ እረፍት ባገኘሁ።" አለ። በዙሪያው ያሉ ሰዎች በዚህ ንግግሩ ላይ ያነወሩት መሰሉ። በዚህ ጊዜም እንዲህ አለ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: 'ቢላል ሆይ! የሶላትን አዛንና ኢቃም አድርግ በርሷ እረፍት እንድናገኝ!'" ይህም ሶላት ውስጡ አላህን ማናገር፣ ለነፍስና ለቀልብ እርካታ ስላለው ነው።