+ -

عن أبي مالكٍ الأشعريِّ رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«الطُّهُورُ شَطْرُ الْإِيمَانِ، وَالْحَمْدُ لِلهِ تَمْلَأُ الْمِيزَانَ، وَسُبْحَانَ اللهِ وَالْحَمْدُ لِلهِ تَمْلَآنِ -أَوْ تَمْلَأُ- مَا بَيْنَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ، وَالصَّلَاةُ نُورٌ، وَالصَّدَقَةُ بُرْهَانٌ، وَالصَّبْرُ ضِيَاءٌ، وَالْقُرْآنُ حُجَّةٌ لَكَ أَوْ عَلَيْكَ، كُلُّ النَّاسِ يَغْدُو، فَبَايِعٌ نَفْسَهُ فَمُعْتِقُهَا أَوْ مُوبِقُهَا».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 223]
المزيــد ...

አቢ ማሊክ አልአሽዐሪይ - አላህ መልካም ሥራቸው ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ:
"ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል ፤ ሰላት ብርሃን ነው፣ ምጽዋት ማስረጃ ነው፣ ትዕግስት ወገግታ (አንፀባራቂ ብርሃን) ነው፣ ቁርኣን ላንተ ወይም በአንተ ላይ ማስረጃ ነው። ሁሉም ሰው በማለዳ ወጥቶ ነፍሱን ይሸጣል። ወይ ከጥፋት ነፃ ያወጣታል ወይም ወደ ጥፋት ይጥላታል። "

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 223]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ውጫዊ ንፅህና በውዱ እና በገላ ትጥበት የሚተገበር እንደሆነና የሰላት ቅድመ መስፈርት እንደሆነም ይነግሩናል ። "አልሐምዱሊላህ ሚዛንን ትሞላለች " የሚለው ነቢያዊ ንግግር :- ጥራት ይገባውና አላህን ማወደስ እንዲሁም ምሉዕ በሆኑ ባህሪያቶች እሱን መግለፅ፥ የትንሳኤ ቀን ስትመዘን የስራዎችን ሚዛን ትሞላለች ማለት ነው። "ሱብሐነላህ ወልሐምዱሊላህ " የሚለውን መናገር አላህን ከሁሉም ጉድለት ማጥራትና እሱን ከመውደድና ማላቅ ጋር ለግርማው የሚመጥን በሆነ የተሟላ ምሉዕነት መግለፅ ሲሆን በሰማያትና ምድር መሀል ያለውንም ይሞላል። "ሰላት ብርሃን ነው። " ለአንድ ሰው ለቀልቡም፣ ለፊቱም ፣ በቀብሩም ውስጥ ፣ በትንሳኤ ቀንም ብርሃን ይሆንለታል። "ምፅዋት ማስረጃ ነው።" ምፅዋት የአንድ አማኝ ኢማን እውነተኝነትንና ለምፅዋት የተገባውን ቃልኪዳን ባለማመኑ ምፅዋት ከመስጠት ከሚታቀበው ሙናፊቅ ተቃራኒ መሆኑንም የሚጠቁም ማስረጃ ነው። "ትእግስት (አንፀባራቂ ብርሃን) ወገግታ ነው።" ትእግስት ማለት ነፍስን ከትእግስት ማጣትና መበሳጨት መቆጣጠር ሲሆን ትእግስት እንደ ፀሀይ ብርሀን ሀሩርና ማቃጠል አብሮት የሚኖር ብርሃን ነው። ምክንያቱም መታገስ ነፍስን መታገልና ከዝንባሌዋ ማቀብ የሚፈልግ ስለሆነ አስቸጋሪ ነው። ታጋሽ ሰው ብርሃናማ፣ የተመራና በትክክለኛነት ላይ ዘውታሪ ከመሆን አይወገድም። ትእግስት ሲባል አላህን በመታዘዝ ላይ ፣ አላህን ከመወንጀል በመራቅ ላይ መታገስ እና ከመከራና አለማዊ የችግር ዓይነቶች ላይ መታገስ ነው። ቁርኣንን ማንበብና ተግባራዊ በማድረግ ምክንያት "ቁርኣን ላንተ ማስረጃ ነው።" ወይም በሱ ሳይሰሩና ሳያነቡ ቁርኣንን በመተዉ ምክንያት "በአንተ ላይ ማስረጃ ይሆናል።" ቀጥሎ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰዎች ሁሉ እንደሚለፉ፣ ለተለያዩ ተግባራትም እንደሚበታተኑ፣ ከእንቅልፋቸው በመንቃት ለተለያዩ ተግባራት ከቤቶቻቸው እንደሚወጡ ተናገሩ። ከነሱም መካከል በአላህ ትእዛዝ ላይ በመፅናት ነፍሱን ከእሳት ነፃ የሚያወጣ ሲኖር ፤ ከነሱም ውስጥ ከዚህ የአላህ ትእዛዝ በመዘንበል ወንጀል ውስጥ የሚወድቅና ነፍሱ እሳት ውስጥ በመግባቷ ለጥፋት የሚዳርጋት አለ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ንፅህና ሁለት አይነት ነው። ውጫዊ ንፅህና በዉዱእ እና በገላ ትጥበት ሲሆን፤ ውስጣዊ ንፅህና ደግሞ በተውሒድ፣ በኢማንና መልካም ስራ የሚመጣ ነው።
  2. ሰላት ለአንድ ባሪያ በዱንያም ሆነ በትንሳኤ ቀን ብርሃን ስለሆነ ሰላትን በጥንቃቄ መስገድ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
  3. ምፅዋት የእውነተኛ ኢማን ማስረጃ ነው።
  4. ቁርኣን በአንተ ላይ ሳይሆን ለአንተ ማስረጃ እንዲሆን ቁርኣንን መተግበር እና ማመን አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
  5. ነፍስ በአምልኮ ካልጠመድካት በወንጀል ታጠምድሀለች።
  6. ሁሉም ሰው መስራቱ የማይቀር ጉዳይ ነው። ወይ ነፍሱን በአምልኮ ነፃ ያወጣታል ወይም በወንጀል ለጥፋት ይዳርጋታል።
  7. ትዕግስት እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ቻይነትንና ምንዳን ከአላህ ማሰብ ይፈልጋል።
ተጨማሪ