عن بريدة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«إِنَّ الْعَهْدَ الَّذِي بَيْنَنَا وَبَيْنَهُمُ الصَّلَاةُ، فَمَنْ تَرَكَهَا فَقَدْ كَفَرَ».
[صحيح] - [رواه الترمذي والنسائي وابن ماجه وأحمد] - [سنن النسائي: 463]
المزيــد ...
ከቡረይደህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነኑ ነሳኢይ - 463]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሙስሊሞችና በሌሎች ከሀዲያንና መናፍቃን መካከል ያለው መተማመኛና ቃል ኪዳን ሶላት እንደሆነና ሶላትን የተወ ሰውም በርግጥ እንደካደ ገለፁ።