عن جابرٍ رضي الله عنه قال: سمعت النبي صلى الله عليه وسلم يقول:
«إِنَّ بَيْنَ الرَّجُلِ وَبَيْنَ الشِّرْكِ وَالْكُفْرِ تَرْكَ الصَّلَاةِ».

[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...

ከጃቢር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ፦
'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'"

Sahih/Authentic. - [Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግዴታ ሶላትን ከመተው አስጠነቀቁ። በሰውዬውና ሺርክና ክህደት ላይ በመውደቅ መካከል ያለው ግርዶ ሶላትን መተው እንደሆነም ተናገሩ። ሶላት ከኢስላም ማእዘናቶች መካከል ሁለተኛው ማእዘን ነው፣ በኢስላም ትልቅ ጉዳይ ነው። ግዴታነቱን አስተባብሎ የተወ ሰው በሁሉም ዑለማእ (የኢስላም ሊቃውንት) ስምምነት መሰረት ክዷል። በስንፍናና ድክመት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ የተወም እንደዚሁ ከሀዲ ነው። በዚህ ዙሪያ የሶሐቦች ሙሉ ስምምነት እንዳለም ተሰምቷል። አንዳንዴ የሚተው አንዳንዴ የሚሰግድ ከሆነ ደግሞ ለዚህ ከባድ ዛቻ የተጋረጠ ይሆናል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሶላትና በርሱ ላይ መጠባበቅ ያለውን አንገብጋቢነት እንረዳለን። ሶላት በክህደትና ኢማን መካከል ያለ መለያ ነው።
  2. ሶላትን የተወና ያጓደሉ ሰው ላይ ብርቱ ማስጠንቀቂያ መምጣቱን እንረዳለን።
ተጨማሪ