عَنْ أَبِي حُمَيْدٍ أَوْ عَنْ أَبِي أُسَيْدٍ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمُ الْمَسْجِدَ فَلْيَقُلِ: اللَّهُمَّ افْتَحْ لِي أَبْوَابَ رَحْمَتِكَ، وَإِذَا خَرَجَ فَلْيَقُلِ: اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنْ فَضْلِكَ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 713]
المزيــد ...
ከአቡ ሑመይድ ወይም አቡ ኡሰይድ እንደተዘገበው እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል።›"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 713]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ በሚገባ ወቅት የሚባለውን ዱዓ ለኡመታቸው ጠቆሙ። (አልላሁምመ ኢፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲክ) (አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) የእዝነትን ምክንያቶች ለርሱ እንዲያመቻችለት አላህን ይጠይቃል። ከመስጂድ ለመውጣት የፈለገ ጊዜም (አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ) (አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል። አላህን ከችሮታውና ከሐላል ሲሳዩ ተጨማሪ ፀጋዎቹን ይጠይቃል።