عَنْ أَبِي قَتَادَةَ السَّلَمِيِّ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمُ الْمَسْجِدَ فَلْيَرْكَعْ رَكْعَتَيْنِ قَبْلَ أَنْ يَجْلِسَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 444]
المزيــد ...
ከአቡ ቀታዳ አስሰለሚይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ ይስገድ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 444]
በማንኛውም ወቅትና ለማንኛውም አላማ መስጂድ የመጣና የገባ ሰው ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ እንዲሰግድ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አነሳሱ። ይሀውም ሁለቱ የተሒየተል መስጂድ ረከዓዎች ናቸው።