+ -

عَنِ ابْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ:
حَفِظْتُ مِنَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَشْرَ رَكَعَاتٍ: رَكْعَتَيْنِ قَبْلَ الظُّهْرِ، وَرَكْعَتَيْنِ بَعْدَهَا، وَرَكْعَتَيْنِ بَعْدَ المَغْرِبِ فِي بَيْتِهِ، وَرَكْعَتَيْنِ بَعْدَ العِشَاءِ فِي بَيْتِهِ، وَرَكْعَتَيْنِ قَبْلَ صَلاَةِ الصُّبْحِ، وَكَانَتْ سَاعَةً لاَ يُدْخَلُ عَلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِيهَا، حَدَّثَتْنِي حَفْصَةُ أَنَّهُ كَانَ إِذَا أَذَّنَ المُؤَذِّنُ وَطَلَعَ الفَجْرُ صَلَّى رَكْعَتَيْنِ، وَفِي لَفْظٍ: أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يُصَلِّي بَعْدَ الْجُمُعَةِ رَكْعَتَيْنِ.

[صحيح] - [متفق عليه بجميع رواياته] - [صحيح البخاري: 1180]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
"ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ። እነርሱም ከዙህር በፊት ሁለት ረከዓ፣ ከዙህር በኋላም ሁለት ረከዓ፣ ከመጝሪብ በኋላ ቤታቸው ውስጥ ሁለት ረከዓ፣ ከዒሻእ በኋላም ቤታቸው ውስጥ ሁለት ረከዓ፣ ከሱብሒ ሶላት በፊት ሁለት ረከዓ ናቸው። የሱብሒ ወቅት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ የማይገባባት ሰአት ነበረች። ስለሰአቲቱም ሙአዚኑ አዛን ያለ ጊዜና ጎህ የወጣ ጊዜ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ እንደነበር ሐፍሷ ነገረችኝ።" በሌላ ዘገባ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጁመዓ ሶላት በኋላም ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] - [በሁሉም ዘገባዎቹ ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1180]

ትንታኔ

ዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዺየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሸመደዱትን አስር የሱና ረከዓዎች ገለጹ። እነዚህ ሱናዎች "ሱነን አርረዋቲብ" (ከግዴታ ሶላት በፊት ወይም በኋላ የሚሰገዱ ሱና ሶላቶች) ተብለው ይጠራሉ። ሁለት ረከዓ ከዙህር በፊትና ሁለት ረከዓ ከዙህር በኋላ፤ ከመጝሪብ በኋላ ሁለት ረከዓ ቤታቸው ውስጥ፤ ሁለት ረከዓ ከዒሻ ሶላት በኋላ ቤታቸው ውስጥ፤ ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር። ይህም አስር ረከዓ ሞላ። ከጁመዓ ሶላት በኋላም ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. እነዚህ ከፈርድ በፊትና በኋላ የሚሰገዱ ሶላቶች ተወዳጅ መሆናቸውንና በነርሱ ላይ መዘውተርም እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. ሱና ሶላቶችን ቤት ውስጥ መፈፀም መደንገጉን እንረዳለን።