عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ مُغَفَّلٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم:
«بَيْنَ كُلِّ أَذَانَيْنِ صَلَاةٌ، بَيْنَ كُلِّ أَذَانَيْنِ صَلَاةٌ» ثُمَّ قَالَ فِي الثَّالِثَةِ: «لِمَنْ شَاءَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 627]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ሙገፈል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"በየሁሉም ሁለት አዛኖች መካከል ሶላት አለ። በየሁሉም ሁለት አዛኖች መካከል ሶላት አለ።" ቀጥለው በሶስተኛው "ለፈለገ ሰው" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 627]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በየሁሉም አዛንና ኢቃም መካከል ሱና ሶላት እንዳለ ገለፁ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ደጋገሙት። በሶስተኛውም ይህን ሶላት መስገድ ለፈለገ ሰው ተወዳጅ እንደሚሆንለት ተናገሩ።