عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِذَا سَمِعْتُمُ النِّدَاءَ، فَقُولُوا مِثْلَ مَا يَقُولُ المُؤَذِّنُ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"(የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙአዚንን በምንሰማ ጊዜ ለርሱ ጥሪ መልስ በመስጠት ላይ አነሳሱ (አበረታቱ)። ምላሹም በየአንዳንዱ አረፍተ ነገር ሙአዚኑ የሚለውን በማለት ነው። ተክቢራው በሚያደርግ ጊዜ እኛም ከርሱ በኋላ ተክቢራ እናደርጋለን፣ ሁለቱን የምስክር ቃላት (ሸሀደተይንን) በሚል ጊዜ እኛም ከርሱ በኋላ እንላለን፣ (ሐይየ ዐለስ-ሶላህና ሐይየ ዐለል ፈላሕ) የሚሉት ሁለቱ አረፍተ ነገሮች ግን ይለያሉ። ከነርሱ በኃላ የምንለው "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ" (ብልሃትም ሆነ ኃይል ከአላህ ውጪ የለም) ነውና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሐዲሱ ጥቅል መልዕክት ስለሚያስፈርድ አዛን ባዮች ከበዙ የመጀመሪያው ሙአዚን አዛን ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለተኛውንም ሙአዚን አዛን ተከትሎ ለጥሪው መልስ ይሰጣል።
  2. መፀዳጃ ቤት ውስጥ ወይም እየተፀዳዳ እስካልሆነ ድረስ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆን ለሙአዚን ጥሪ መልስ መሰጠት አለበት።