عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما قَالَ:
مَرَّ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِقَبْرَيْنِ، فَقَالَ: «إِنَّهُمَا لَيُعَذَّبَانِ، وَمَا يُعَذَّبَانِ فِي كَبِيرٍ، أَمَّا أَحَدُهُمَا فَكَانَ لاَ يَسْتَتِرُ مِنَ البَوْلِ، وَأَمَّا الآخَرُ فَكَانَ يَمْشِي بِالنَّمِيمَةِ» ثُمَّ أَخَذَ جَرِيدَةً رَطْبَةً، فَشَقَّهَا نِصْفَيْنِ، فَغَرَزَ فِي كُلِّ قَبْرٍ وَاحِدَةً، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللَّهِ، لِمَ فَعَلْتَ هَذَا؟ قَالَ: «لَعَلَّهُ يُخَفِّفُ عَنْهُمَا مَا لَمْ يَيْبَسَا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 218]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለት ቀብሮች በኩል አለፉና እንዲህ አሉ ' እነርሱ እየተቀጡ ነው። (በናንተ እይታ) ትልቅ በሆነ ወንጀልም አይደለም የሚቀጡት። አንደኛቸው ከሽንት አይጥራራም ነበር። ሌላኛው ደግሞ ነገር በማመላለስ የሚዞር ነበር።' ቀጥለውም እርጥብ ቅጠል በመያዝ ለሁለት ሰነጠቁትና በእያንዳንዱ ቀብር ላይ አንድ አንድ ተከሉ። ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለምን ይህን ፈፀሙ?' ብለው ጠየቁ። እርሳቸውም ‘ቅጠሎቹ እስካልደረቁ ድረስ ከነርሱ ላይ ቅጣቱን ያቀልላቸዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።' ብለው መለሱ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 218]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለት ቀብሮች በኩል አለፉና እንዲህ አሉ፦ የነዚህ ሁለት ቀብር ባለቤቶች እየተቀጡ ነው። አላህ ዘንድ ትልቅ ወንጀል ቢሆንም በናንተ እይታ ግን ትልቅ በሆነ ወንጀል አይደለም የሚቀጡት። አንደኛው: በሚፀዳዳ ወቅት ሰውነቱንና ልብሱን ከሽንት መጠበቅን ትኩረት አይሰጠውም ነበር። ሌላኛው ደግሞ በሰዎች መካከል ነገር በማመላለስ ይዞር ነበር። በሰዎች መካከል መጎዳዳትን፣ ልዩነትን ማምጣትና ሀሜትን አስቦ የሌላን ሰው ነገር ያዋስድ ነበር።