+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ قَالَ: خَرَجَ مُعَاوِيَةُ عَلَى حَلْقَةٍ فِي الْمَسْجِدِ، فَقَالَ: مَا أَجْلَسَكُمْ؟ قَالُوا: جَلَسْنَا نَذْكُرُ اللهَ، قَالَ آللَّهِ مَا أَجْلَسَكُمْ إِلَّا ذَاكَ؟ قَالُوا: وَاللهِ مَا أَجْلَسَنَا إِلَّا ذَاكَ، قَالَ: أَمَا إِنِّي لَمْ أَسْتَحْلِفْكُمْ تُهْمَةً لَكُمْ، وَمَا كَانَ أَحَدٌ بِمَنْزِلَتِي مِنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَقَلَّ عَنْهُ حَدِيثًا مِنِّي:
وَإِنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ خَرَجَ عَلَى حَلْقَةٍ مِنْ أَصْحَابِهِ، فَقَالَ: «مَا أَجْلَسَكُمْ؟» قَالُوا: جَلَسْنَا نَذْكُرُ اللهَ وَنَحْمَدُهُ عَلَى مَا هَدَانَا لِلْإِسْلَامِ، وَمَنَّ بِهِ عَلَيْنَا، قَالَ: «آللَّهِ مَا أَجْلَسَكُمْ إِلَّا ذَاكَ؟» قَالُوا: وَاللهِ مَا أَجْلَسَنَا إِلَّا ذَاكَ، قَالَ: «أَمَا إِنِّي لَمْ أَسْتَحْلِفْكُمْ تُهْمَةً لَكُمْ، وَلَكِنَّهُ أَتَانِي جِبْرِيلُ فَأَخْبَرَنِي أَنَّ اللهَ عَزَّ وَجَلَّ يُبَاهِي بِكُمُ الْمَلَائِكَةَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2701]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ሙዓዊያ በመስጂድ ውስጥ ክብ በሰሩ ሰዎች ላይ መጣና "ምንድን ነው ያስቀመጣችሁ?" አላቸው። እነርሱም "የተቀመጥነው አላህን ልናወሳ ነው።" አሉ። እርሱም "በአላህ ስም ማሉልኝ ከዚህ በቀር ሌላ አላስቀመጣችሁምን?" አላቸው። እነርሱም "በአላህ እንምላለን ከርሱ በቀር ሌላ አላስቀመጠንም።" አሉ። እርሱም "ያስማልኳችሁ ጠርጥሬያችሁ ሳይሆን በኔ ደረጃ ላይ ያለ ሆኖ ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከኔ ያነሰ የሐዲስ ብዛት የዘገበ የለም።
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ክብ በሰሩ ባልደረቦቻቸው ላይ መጡና ‹ምንድን ነው ያስቀመጣችሁ?› አሉ። እነርሱም ‹የተቀመጥነው አላህን ልናወሳውና ለኢስላም ስለመራንና ኢስላምን ለኛ ስለለገሰን ልናመሰግነው ነው።› አሉ። እርሳቸውም ‹በአላህ ስም ማሉልኝ ከዚህ በቀር ሌላ አላስቀመጣችሁምን?› አሏቸው። እነርሱም ‹በአላህ እንምላለን ከርሱ በቀር ሌላ አላስቀመጠንም።› አሉ። እርሳቸውም ‹ጠርጥሬያችሁ አይደለም ያስማልኳችሁ። ነገር ግን ጂብሪል መጥቶ አላህ በናንተ መላእክትን እንደሚፎካከር ስለነገረኝ ነው።› አሉ።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2701]

ትንታኔ

ሙዓዊያ ቢን አቡ ሱፍያን (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና መስጂድ ውስጥ ክብ ወደሰሩ ሰዎች መጡና ለምን ጉዳይ እንደተሰበሰቡ ጠየቃቸው። እነርሱም "አላህን እያወሳን ነው።" አሉ። ሙዓዊያም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና በመቀመጣቸውና በመሰብሰባቸው አላህን ከማውሳት በቀር ሌላን እንዳልፈለጉ አስማሏቸው። እነርሱም ማሉላቸው። ቀጥሎ "በእውነተኝነታችሁ ላይ ጠርጥሬያችሁ አይደለም ያስማልኳችሁ።" አሏቸው። ቀጥሎም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እንደርሱ ቅርብ የነበረና የርሱ ቅርበት እህቱ ኡሙ ሐቢባም የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሚስት ስለነበረችና እርሱም ወሕይ ፀጸሐፊ ስለነበረ ነው። ከመሆኑም ጋር ግን ጥቂት ሐዲስ ያስተላለፈው እርሱ እንደነበር ተናገረ። አንድ ቀን ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከቤታቸው እንደወጡና መስጂድ ውስጥ ተቀምጠው አላህን እያወሱ፤ አላህ ለእስልምና ስለመራቸውና እስልምናን ስለለገሳቸውም እያመሰግኑት አግኝተዋቸው ልክ ሙዓዊያ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ባልደረቦቹን እንዳስማላቸው ሁሉ ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጠይቀው እንዳስማሏቸው ተናገረ። ቀጥሎም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነርሱን የጠየቁበትንና ያስማሉበትን ምክንያት ተናገሩ። እርሱም መልዐኩ ጂብሪል የአላህ ሰላም በርሱ ላይ ይስፈንና እርሳቸው ጋር መጥቶ አላህ በናንተ መላእክቱን እንደሚፎካከር የናንተንም ደረጃ ለነርሱ እንደሚገልፅ፣ የስራችሁን ውበት እንደሚያሳያቸውና እነርሱ ዘንድም በናንተ ላይ እንደሚያወድስ ነገረኝ አሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሙዓዊያ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው ያላቸው ደረጃና ዕውቀትን በማድረስ ዙሪያ በአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመከተል ጉጉታቸውን እንረዳለን።
  2. ያለምንም ክፉ ጥርጣሬ የጉዳዩን አንገብጋቢነትን ለማስገንዘብ ሲባልም ማስማል እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  3. የዚክርና ዕውቀት ለመቅሰም የመቀማመጦችን ደረጃ፤ አላህም እንደሚወደውና መላዕክቶችንም በዚህ ስራቸው እንደሚፎካከርበት እንረዳለን።