عن أبي موسى الأشعري رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ حَمَلَ عَلَيْنَا السِّلَاحَ فَلَيْسَ مِنَّا».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 7071]
المزيــد ...

ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"መሳሪያውን በኛ ላይ ያነሳ ከኛ አይደለም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 7071]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለማስፈራራት ወይም ንብረታቸውን ለመቀማት በሙስሊሞች ላይ መሳሪያ ከማንሳት አስጠነቀቁ። ያለ አግባብ ይህንን የፈፀመም ትልቅ ሀጢአትንና ወንጀልን መፈፀሙን ለዚህ ከባድ ዛቻም መጋረጡን አሳሰቡ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሙስሊም ከሙስሊም ወንድሙ ጋር መጋደሉ ብርቱ ማስጠንቀቂያ የመጣበት ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
  2. በምድር ላይ ከሚሰሩ ትላልቅ ወንጀሎችና ብክለቶች መካከል መሳሪያን በሙስሊሞች ላይ ማንሳትና በመግደል ማበላሸት አንዱ ነው።
  3. የተጠቀሰው ዛቻ ወሰን አላፊዎችን፣ አጥፊዎችንና ሌሎችም የመሳሰሉትን በሀቅ (በሸሪዓ በተፈቀደ ምክንያት) መጋደልን አያካትትም።
  4. ለቀልድ እንኳ ቢሆን ሙስሊሞችን በመሳሪያ ወይም በሌላ ነገር ማስፈራራት መከልከሉን እንረዳለን።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (58)
ተጨማሪ