+ -

عَنْ ابنِ عُمَرَ رَضيَ اللهُ عنهما عَنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنِ اقْتَنَى كَلْبًا إِلَّا كَلْبَ ضَارٍ أَوْ مَاشِيَةٍ نَقَصَ مِنْ عَمَلِهِ كُلَّ يَوْمٍ قِيرَاطَانِ»، قَالَ سَالِمٌ: وَكَانَ أَبُو هُرَيْرَةَ يَقُولُ: «أَوْ كَلْبَ حَرْثٍ»، وَكَانَ صَاحِبَ حَرْثٍ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1574]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ:
«"ከአዳኝ ወይም ከከብት ጠባቂ ውሻ ውጪ የሆነ ውሻን ያሳደገ ሰው በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጦች ይቀነሱበታል።" ሳሊም እንዲህ አለ: አቡ ሁረይራም የእርሻ ባለቤት ነበርና "ወይም የእርሻ ጠባቂ ውሻ ካልሆነ" ይል ነበር።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1574]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለአደን ወይም ለከብቶችና አዝርዕት ጥበቃ ፈልጎ ካልሆነ በቀር ውሻን ከማሳደግ ከለከሉ። ከነዚህ ውጪ ለሆነ አላማ ያሳደገ ሰውም በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጥ ምንዳ ይቀነስበታል። ቂራጥ ሲባል የተፈለገው መጠንን የሚያውቀውም አላህ ብቻ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አንድ ሙስሊም ከተገደቡለት አላማዎች ውጪ ውሻን ማሳደግ አይፈቀድለትም።
  2. ውሻ ብዙ ጉዳትና ብልሽት ስለሚያስከትል ማሳደጉ የተከለከለ ነው። ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንደተረጋገጠው መላእክቶች ውሻ ያለበት ቤት ውስጥ አይገቡም። በተጨማሪም ውሻ ውስጥ ደጋግሞ በውሃና አፈር በማጠብ ካልሆነ በቀር የማይወገድ ከባድ ነጃሳ አለ።
ተጨማሪ