+ -

عَنِ الْبَرَاءِ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
مَا رَأَيْتُ مِنْ ذِي لِمَّةٍ أَحْسَنَ فِي حُلَّةٍ حَمْرَاءَ مِنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، شَعْرُهُ يَضْرِبُ مَنْكِبَيْهِ، بَعِيدَ مَا بَيْنَ الْمَنْكِبَيْنِ، لَيْسَ بِالطَّوِيلِ وَلَا بِالْقَصِيرِ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2337]
المزيــد ...

ከበራእ- አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
"ባለረዥም ፀጉር ሁኖ ቀያይ መስመር ያለበትን ጥቁር አለባሽ ልብስ የሚያምርበት ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የበለጠ እጅግ ውብ ሰው አልተመለከትኩም። ፀጉራቸው ትከሻቸውን ይመታ ነበር። በሁለቱ ትከሻዎቻቸው መካከል መራራቅ አለ። ረጅምም አጭርም አይደሉም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2337]

ትንታኔ

በራእ ቢን ዓዚብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የበለጠ ከርዝመቱ የተነሳ ፀጉሩ ትከሻው ድረስ የደረሰና ቀያይ መስመሮች ያሉበት ጥቋቁር ሽርጥና ኩታ የለበሰ አንድም እጅግ ውብ ሰው አልተመከትኩም ብለው ተናገሩ። በተጨማሪም ከርሳቸው አካላዊ ተፈጥሮ መካከል በሁለቱ ትከሻዎቻቸው መካከል መራራቅ እንዳለ፣ ደረታቸው ሰፊና ቁመታቸው አጭርም ረጅምም ሳይሆን መካከለኛ ቁመት እንደሆነ ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. እንደ ፀጉር ማማር፣ የደረት መስፋት፣ ያማረ ተክለ ቁመናና ከዚህ ውጪም ያሉ ጥቂት የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ውብ የሆኑን ውጫዊ ባህሪያቶች ተብራርተው እናያለን።
  2. የተከበሩት ሶሓቦች (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያላቸውን ውዴታ እንመለከታለን። ውዴታቸው ከነርሱ በኋላ ለመጡት ትውልዶች ስለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) አካላዊና ውስጣዊ ባህሪያትና ሁለንተናዊ መገለጫ እስከመተረክና እስከማስተላለፍ የደረሰ ነበር።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الغوجاراتية الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ