عَنْ أَبِي بُرْدَةَ الْأَنْصَارِيِّ رَضيَ اللهُ عنهُ أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«لَا يُجْلَدُ أَحَدٌ فَوْقَ عَشَرَةِ أَسْوَاطٍ إِلَّا فِي حَدٍّ مِنْ حُدُودِ اللهِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1708]
المزيــد ...
ከአቡ ቡርዳህ አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰማ፦
"(አላህን በማመፁ ምክንያት) አላህ ያስቀመጠው የቅጣት ወሰን ካልሆነ በቀር (ስርአት ለማስያዝ) ተብሎ አንድም ሰው ከአስር አለንጋ በላይ እንዳይገረፍ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1708]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በወንጀል ላይ ካልሆነ በቀር አንድም ሰው ከአስር አለንጋ በላይ መገረፉን ከለከሉ። ሐዲሡ ውስጥ የተፈለገው በቁጥር ተገድበው ከአላህና ከመልክተኛው የመጡ ግርፋቶች ወይም ምቶች ወይም ልዩ ቅጣቶችን አይደለም። ይልቁንም በሐዲሡ የተፈለገው ስርአት ለማስያዝ ሲባል ሚስትንና ልጅን መግረፍ ቢያስፈልግ ከአስር አለንጋ አይጨምር ማለት ነው።