+ -

عَنْ عَلِيٍّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ أَصَابَ حَدًّا فَعُجِّلَ عُقُوبَتَهُ فِي الدُّنْيَا فَاللَّهُ أَعْدَلُ مِنْ أَنْ يُثَنِّيَ عَلَى عَبْدِهِ العُقُوبَةَ فِي الآخِرَةِ، وَمَنْ أَصَابَ حَدًّا فَسَتَرَهُ اللَّهُ عَلَيْهِ وَعَفَا عَنْهُ فَاللَّهُ أَكْرَمُ مِنْ أَنْ يَعُودَ فِي شَيْءٍ قَدْ عَفَا عَنْهُ».

[حسن] - [رواه الترمذي وابن ماجه] - [سنن الترمذي: 2626]
المزيــد ...

ከዐሊይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ሸሪዓዊ የምድር ቅጣት የተወሰነለትን ወንጀል የፈፀመና ቅጣቱም በዱንያ ተፈፃሚ የሆነበት ሰው አላህ በመጪውም አለም ባሪያውን በድጋሚ ከመቅጣት የላቀ ፍትሃዊ ነው። ሸሪዓዊ የምድር ቅጣት የተወሰነለትን ወንጀል የፈፀመ አላህም ለርሱ ምድር ላይ ሸሽጎለት ይቅር ካለው በኃላ አላህ ይቅር ያለውን አንዳች ነገር ወደ ኋላ ተመልሶ ከመቅጣትም የላቀ እጅግ ቸር ነው።"

[ሐሰን ነው።] - [ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2626]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንደዝሙትና ስርቆት የመሰሉ ሸሪዓዊ የምድር ቅጣቶችን የሚያስፈርዱ ወንጀሎችን የፈፀመ ሰውና ቅጣቱን በምድር መቅጫ ሸሪዓው ህግ መሰረት የተቀጣ ይህ መቀጣቱ የተቀጣባትን ወንጀል እንደሚያብስለት፤ በመጪው አለም ያለበትንም ቅጣት እንደሚያስነሳለት ተናገሩ። ምክንያቱንም ሲገልፁ አላህ በባሪያው ላይ ሁለት ቅጣቶችን ሰብስቦ ከመቅጣት የላቀ አዛኝና ቸር ነው አሉ። አላህ በዱንያ ወንጀሉን የሸሸገለት፤ በዛ ወንጀሉም ያልቀጣው፤ አላህ ይቅር ያለውና የማረው ሰውም አላህ ዐዘ ወጀል የማረውንና ይቅር ያለውን ወንጀል ወደ ኋላ ተመልሶ ከመቅጣትም የላቀ የተከበረና ቸር ነው አሉ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የአላህን ፍትህ፣ ቸርነትና እዝነቱ ትልቅነቱን እንረዳለን።
  2. በምድር ውስጥ በሸሪዓ መቅጫ ህግ መሰረት መቀጣት ወንጀልን እንደሚያስምር እንረዳለን።
  3. የሸሪዓ መቅጫ ህግ ያለው ወንጀል ላይ የወደቀ ሰው አላህ እንደሸሸገው ነፍሱንም መሸሸግና ወደ ንፁህ ተውበት መቻኮል ይገባዋል።
ትርጉም: እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ሲንሃላዊ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ተጨማሪ