عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«بَدَأَ الْإِسْلَامُ غَرِيبًا، وَسَيَعُودُ كَمَا بَدَأَ غَرِيبًا، فَطُوبَى لِلْغُرَبَاءِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 145]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"እስልምና እንግዳ ሆኖ ጀመረ። ልክ እንደጀመረውም ወደ እንግዳነት ይመለሳል። ለእንግዶቹ 'ጡባ' ይሰጣቸዋል (አለላቸው)።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 145]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እስልምና በተወሰኑ ሰዎች፣ በአናሳ ተከታዮች እንግዳ ሆኖ ጀመረ። ልክ እንደጀመረውም እስልምናን የሚተገብር በማነሱ ወደ እንግዳነት ይመለሳል። ሃሴት፣ ያማረ ሁኔታና የአይን ማረፊያ ለእንግዶቹ አለላቸው አሉ።