+ -

عَنْ عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، وَكَانَ شَهِدَ بَدْرًا، وَهُوَ أَحَدُ النُّقَبَاءِ لَيْلَةَ العَقَبَةِ: أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ، وَحَوْلَهُ عِصَابَةٌ مِنْ أَصْحَابِهِ:
«بَايِعُونِي عَلَى أَلَّا تُشْرِكُوا بِاللَّهِ شَيْئًا، وَلاَ تَسْرِقُوا، وَلاَ تَزْنُوا، وَلاَ تَقْتُلُوا أَوْلاَدَكُمْ، وَلاَ تَأْتُوا بِبُهْتَانٍ تَفْتَرُونَهُ بَيْنَ أَيْدِيكُمْ وَأَرْجُلِكُمْ، وَلاَ تَعْصُوا فِي مَعْرُوفٍ، فَمَنْ وَفَى مِنْكُمْ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ، وَمَنْ أَصَابَ مِنْ ذَلِكَ شَيْئًا فَعُوقِبَ فِي الدُّنْيَا فَهُوَ كَفَّارَةٌ لَهُ، وَمَنْ أَصَابَ مِنْ ذَلِكَ شَيْئًا ثُمَّ سَتَرَهُ اللَّهُ فَهُوَ إِلَى اللَّهِ، إِنْ شَاءَ عَفَا عَنْهُ وَإِنْ شَاءَ عَاقَبَهُ» فَبَايَعْنَاهُ عَلَى ذَلِكَ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 18]
المزيــد ...

ከዑባዳ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: በድር ዘመቻ ከተሳተፉት ሶሐቦች መካከል አንዱ ነበር። የዓቀባው ምሽት ከነበሩ መሪዎችም መካከል አንዱ ልዑክ ነበር። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዙሪያቸው ከባልደረቦቻቸው መካከል የተወሰኑ ስብስቦች ባሉበት እንዲህ አሉ:
«"በአላህ ላይ አንዳችንም ላታጋሩ፤ ላትሰርቁ፤ ዝሙት ላትሰሩ፤ ልጆቻችሁን ላትገድሉ፤ በእጆቻችሁና በእግሮቻችሁ መካከል የምትቀጥፉትን ቅጥፈት ላትፈፅሙ፤ በመልካም ነገር ላታምፁ ቃል ተጋቡኝ! ከናንተ መካከል ቃልኪዳኑን የሞላ ምንዳው አላህ ዘንድ ነው። ከነዚህ ወንጀሎች መካከል አንዳችን የፈፀመና በዱንያ የተቀጣ እርሱ ማስማሪያ ይሆንለታል። ከነዚህ ወንጀሎች መካከል አንዳችን ፈፅሞ ከዚያም አላህ የሸሸገለት የርሱ ጉዳይ የሚመለሰው ወደ አላህ ነው። ከፈለገ ይቅር ይለዋል። ከፈለገም ይቀጣዋል።" እኛም በነዚህ ጉዳዮች ላይ ቃልኪዳን ተጋባናቸው።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 18]

ትንታኔ

ዑባዳ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ትልቁን የበድር ዘመቻ ከተሳተፉት ሶሐቦች መካከል አንዱ ነበር። መልክተኛው በመካ ሳሉ ወደ መዲና ከመሰደዳቸው በፊት ሚና በተደረገው የዓቀባው ምሽት የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለመርዳት እርሳቸውን ቃልኪዳን ለመጋባት ከመዲና ከመጡ የህዝቦቹ መሪዎች መካከል አንዱ ልዑክ ነበር። የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በባልደረቦቻቸው መካከል ተቀምጠው ሳለ ባልደረቦቻቸውን በነዚህ ጉዳዮች ቃልኪዳን እንዲጋቧቸው ፈለጉ። አንደኛ: አላህን በማምለክ ላይ ቅንጣት ታክል ላያጋሩ፤ ሁለተኛ: ላይሰርቁ፤ ሶስተኛ: ፀያፉን የዝሙት ተግባር ላይፈፅሙ፤ አራተኛ: ወንዶች ልጆቻቸውን ድህነትን ፍራቻ ወይም ሴት ልጆቻቸውን ውርደት ፍራቻ እንዳይገድሏቸው፤ አምስተኛ: በእጆቻቸውና በእግሮቻቸው መካከል የሚፈጥሩትን ውሸት እንዳይፈፅሙ፤ ይህም ምንም እንኳ የተቀሩት አካላቶች ቢሳተፉም አብዛኛው ተግባራት የሚፈፀሙት በሁለቱ ስለሆነ ነው። ስድስተኛ: ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመልካም ትእዛዛቸው እንዳያምፁ ነው። ከነርሱ መካከል በዚሁ ቃልኪዳን ላይ የፀናና የዘወተረ ምንዳው አላህ ዘንድ ነው። ከተጠቀሱት ወንጀሎች መካከል ከሽርክ ውጪ የሆኑትን አንዳቸውንም የሰራና ለስራውም ዱንያ ላይ አላህ ባስቀመጠው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ የተቀጣ ሰው ይህ ቅጣት ለርሱ ወንጀሉን ማስማሪያ ማካካሻ ይሆንለታል። ከነዚህ ወንጀሎች መካከል አንዳችን ሰርቶ ከዚያም አላህ የሸሸገለት ሰው የርሱ ጉዳይ የሚመለሰው ወደ አላህ ነው። ከፈለገ ይቅር ይለዋል። ከፈለገም ይቀጣዋል። በቦታው ያሉት ሁሉም ሶሐቦችም በዚህ ላይ ቃል ተጋቧቸው።

ትርጉም: ኢንዶኔዥያኛ ሲንሃላዊ ቬትናማዊ ሃውሳ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ጂሃድ በሙስሊሞች ላይ ግዴታ ከመደረጉ በፊት በመካ የተደረገው የመጀመሪያው የዐቀባ ቃልኪዳን ያካተታቸው ቁምነገሮች መገለፃቸው፤
  2. ሲንዲይ የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "(በማዛችሁ) መልካም ነገር ላታምፁ" ማለት በተመለከተ: «የርሳቸው ሁሉም ትእዛዝ መልካም እንደሆነ ለማንም አይሰወርም። ከመልካም ነገር ውጪ ያዛሉ ተብሎም አይታሰብም። ታዲያ (በመልካም ነገር) ማለታቸው እርሳቸውን መታዘዝ ግዴታ ያደረገባቸውን ምክንያት ለማስገንዘብና ከመልካም ነገር ውጪ ለፍጡር መታዘዝ እንደማይፈቀድ አፅንዖት ለመስጠት ነው። በማንኛውም ሁኔታ ሳይሆን ለመሪ በሚደረግ ቃልኪዳን ጊዜ ብቻ በመልካም ነገር መታዘዝን መስፈርት ማድረግ እንደሚገባም ያስረዳናል።»
  3. ሙሐመድ ቢን ኢስማዒል አትተይሚይና ሌሎችም እንዲህ ብለዋል: "ቃልኪዳን ሲጋቡ ከግድያ አይነቶች ልጅን መግደልን ብቻ ነጥለው የጠቀሱት መግደልም ዝምድና መቁረጥም ስለሆነ እርሱን በመከልከል ረገድ ልዩ ትኩረት መስጠታቸው ተገቢ ስለሆነ ነው። በተጨማሪም በጊዜው በነርሱ መካከል ተሰራጭቶ የነበረ ድርጊት ስለነበረም ነው። እርሱም ሴቶችን ከነህይወት መቅበርና ወንድ ልጆችን ድህነትን ፍራቻ መግደል ነበር። ወይም እነርሱን ለይተው የጠቀሱት እነርሱ ነፍሳቸውን መከላከል የማይችሉ ስለሆኑ ነው።"
  4. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "የዚህ ሐዲሥ ጥቅል ሀሳብ {አላህ በርሱ መጋራትን አይምርም።} በሚለው የአላህ ንግግር የሚገደብ ነው። ከእስልምና የወጣ ሰው በመካዱ ምክንያት ሲገደል መገደሉ ወንጀሉን የሚያስምር አይሆንም።"
  5. ቃዲ ዒያድ እንዲህ ብለዋል: "አብዛኛው ዑለሞች የመቅጫ ህጎች ወንጀልን ያስምራል የሚል አቋም አላቸው።"