عَنْ عُمَرَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ لَبِسَ الحَرِيرَ فِي الدُّنْيَا لَمْ يَلْبَسْهُ فِي الآخِرَةِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5834]
المزيــد ...
ከዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በዱንያ ሐር የለበሰ ሰው በመጪው ዓለም አይለብሰውም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5834]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ሆኖ በዱንያ ሐር የለበሰ ሰው ተውበት እስካላደረገ ድረስ መቀጫ ሊሆነው ዘንድ በመጪው ዓለም እንደማይለብስ ገለፁ።