عَن عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ أَبِي لَيْلَى أَنَّهُمْ كَانُوا عِنْدَ حُذَيْفَةَ، فَاسْتَسْقَى فَسَقَاهُ مَجُوسِيٌّ، فَلَمَّا وَضَعَ القَدَحَ فِي يَدِهِ رَمَاهُ بِهِ، وَقَالَ: لَوْلاَ أَنِّي نَهَيْتُهُ غَيْرَ مَرَّةٍ وَلاَ مَرَّتَيْنِ -كَأَنَّهُ يَقُولُ: لَمْ أَفْعَلْ هَذَا-، وَلَكِنِّي سَمِعْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«لاَ تَلْبَسُوا الحَرِيرَ وَلاَ الدِّيبَاجَ، وَلاَ تَشْرَبُوا فِي آنِيَةِ الذَّهَبِ وَالفِضَّةِ، وَلاَ تَأْكُلُوا فِي صِحَافِهَا، فَإِنَّهَا لَهُمْ فِي الدُّنْيَا وَلَنَا فِي الآخِرَةِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5426]
المزيــد ...
ከዐብዱረሕማን ቢን አቢ ለይላ እንደተላለፈው እነርሱ ሑዘይፋ ዘንድ ነበሩ። የሚጠጣ እንዲሰጡት ሲጠይቅ አንድ እሳት አምላኪ የሚጠጣ (በብር እቃ) ሰጠው። እቃውን (በሑዘይፋ) እጁ ላይ ሲያኖረውም በርሱ ወረወረበትና እንዲህ አለ: "ከአንድና ሁለት ጊዜ በላይ ባልከለክለው ኖር ‐ ይህን አላደርግም ነበር ‐ ነበር። ነገር ግን ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
"የቀጭን ሐርንና የወፍራም ሐርን ልብስ አትልበሱ! በወርቅና ብር እቃ አትጠጡ! በ(ወርቅና ብር) ትሪም አትብሉ! እርሷ በዚህ ዓለም ለነርሱ ናት፤ በመጪው ዓለም ደግሞ ለኛ ናት።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5426]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሐርን ልብስ በየትኛውም አይነቱ ከመልበስ ወንዶችን ከለከሉ። ወንዶችንም ሴቶችንም በወርቅና ብር እቃዎችና መሳሪያ ከመብላትና ከመጠጣት ከለከሉ። ይህም አማኞች በዚህች አለም አላህን ለመታዘዝ እንደራቁት ሁሉ የትንሳኤ ቀን ደግሞ ለአማኞች ብቻ እንደሆነ ተናገሩ። ከነዚህ መካከልም ለከሀዲያኖች በመጪው ዓለም ምንም የላቸውም። ምክንያቱም የአላህን ትእዛዝ በማመፅ ቸኩለው በዚህ ዓለም ህይወታቸው ምርጥ የሚሉትን ነገሮች በመያዝ ስለተጠቀሙ ነው።