عَنْ رَافِعِ بْنِ خَدِيجٍ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ:
كُنَّا مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِذِي الحُلَيْفَةِ، فَأَصَابَ النَّاسَ جُوعٌ، فَأَصَابُوا إِبِلًا وَغَنَمًا، قَالَ: وَكَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي أُخْرَيَاتِ القَوْمِ، فَعَجِلُوا، وَذَبَحُوا، وَنَصَبُوا القُدُورَ، فَأَمَرَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِالقُدُورِ، فَأُكْفِئَتْ، ثُمَّ قَسَمَ، فَعَدَلَ عَشَرَةً مِنَ الغَنَمِ بِبَعِيرٍ فَنَدَّ مِنْهَا بَعِيرٌ، فَطَلَبُوهُ، فَأَعْيَاهُمْ وَكَانَ فِي القَوْمِ خَيْلٌ يَسِيرَةٌ، فَأَهْوَى رَجُلٌ مِنْهُمْ بِسَهْمٍ، فَحَبَسَهُ اللَّهُ، ثُمَّ قَالَ: «إِنَّ لِهَذِهِ البَهَائِمِ أَوَابِدَ كَأَوَابِدِ الوَحْشِ، فَمَا غَلَبَكُمْ مِنْهَا فَاصْنَعُوا بِهِ هَكَذَا»، فَقَالَ أي رافع: إِنَّا نَرْجُو -أَوْ نَخَافُ- العَدُوَّ غَدًا، وَلَيْسَتْ مَعَنَا مُدًى، أَفَنَذْبَحُ بِالقَصَبِ؟ قَالَ: «مَا أَنْهَرَ الدَّمَ، وَذُكِرَ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ فَكُلُوهُ، لَيْسَ السِّنَّ وَالظُّفُرَ، وَسَأُحَدِّثُكُمْ عَنْ ذَلِكَ: أَمَّا السِّنُّ فَعَظْمٌ، وَأَمَّا الظُّفُرُ فَمُدَى الحَبَشَةِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2488]
المزيــد ...
ከራፊዕ ቢን ኸዲጅ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
«በዙል ሑለይፋ ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጋር ነበርን። ሰዎች ለረሃብ ተጋለጡ። ግመሎችና ፍየሎች በምርኮ አግኝተው ነበር።» ራፊዕ እንዲህ አለ: «ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሰዎች ኋላ ነበሩ። (እርሳቸውን ከመጠበቅ) ቸኮሉና አረዱ። ድስጥ ላይም ጣዱ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሲደርሱ ድስጡ እንዲደፋ አዘዙና ተደፋ። ከዚያም ምርኮውን አከፋፈሉ። የአስር ፍየልን ዋጋ በአንድ ግመል እያደረጉ አከፋፈሉ። አንድ ግመል ግን ፈረጠጠ። እርሱን ሲፈልጉም አደከማቸው። በመካከላቸው የነበረው የፈረስ ቁጥርም ትንሽ ነበር። ከመካከላቸው አንድ ሰውዬ በቀስቱ ወጋውና አላህ አቆመላቸው። ቀጥለው ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "እነዚህ (የቤት) እንስሶች እንደ ዱር እንስሶች የዱር ባህሪ አላቸው። ከነርሱ መካከል አልያዝ ብሎ ያሸነፋችሁ ላይ እንደዚሁ አድርጉ።"» ራፊዕ እንዲህ ብሎም ጠየቃቸው: «እኛ ነገ ከጠላት ጋር እንገናኛለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን ወይም እንሰጋለን። የምናርድበት ቢላም የለንም። በተሳለ ቀርከሃ እንረድን? እርሳቸውም: "ከጥርስና ከጥፍር ውጪ ደምን ያፈሰሰና ሲታረድ የአላህ ስም የተወሳበትን ብሉ። የዚህንም ምክንያት እነግራችኋለሁ። ጥርስ የማታርዱበት አጥንት ስለሆነ ነው፤ ጥፍር የማታርዱበት ደግሞ የሐበሾች ስለት ስለሆነ ነው።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2488]
ራፊዕ ቢን ኸዲጅ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በዙል ሑለይፋ ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጋር እንደነበር ተናገረ። ሰዎችንም ረሃብ አጋጠማቸው። ከአጋርያን የማረኩት ፍየሎችና ግመሎች ነበሩ። ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሳያስፈቅዱም ምርኮ ከመከፋፈሉ በፊት ቸኮሉና አረዱ። ድስጥ ላይም ጣዱት። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሰዎች ኋላ ነበሩ። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ያደረጉትን ሲያውቁ ድስጧ እንድትደፋ አዘው ከነመረቁ አስደፉት። ቀጥለው ምርኮዉን አከፋፈሉ። አስር ፍየሎችን በአንድ ግመል ተለዋጭ እያደረጉ አከፋፈሉ። ከነዚህ ግመሎችም አንድ ግመል ሸሸ። የነበራቸው ፈረስ ትንሽ ነበረና እርሱ ላይ መድረስ አቃታቸው። ከመካከላቸው የነበረ አንድ ሰውዬም በቀስት ወጋው። አላህም አቆመላቸው። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "እነዚህ ለማዳ እንስሶችም የዱር ባህሪ አላቸው። ከነርሱ መካከል ለመያዝ ያቃታችሁና ያሸነፋችሁን እንደዚሁ አድርጉት።" ራፊዕም እንዲህ አለ: "እኛ ነገ ጠላትን እንገናኛለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በመሳሪያዎቻችን እንዳናርድ ስለቱን እንዳይጎዳብን ያሰጋናል። ማረዳችን ደግሞ ግድ ነው። እኛ ጋር ደግሞ ቢላ የለንምና በደረቀ ስለታማ ቀርከሃ እንረድን?" ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ከጥርስና ከጥፍር ውጪ ደምን አብዝቶ ያፈሰሰና ሲታረድ የአላህ ስም የተወሳበትን ብሉ። የሁለቱንም ምክንያት እነግራችኋለሁ። ጥርስ የማታርዱበት አጥንት ስለሆነ ነው። ጥፍር የማታርዱበት ደግሞ የሐበሻ ከሃዲዎች ለማረድ የሚጠቀሙበት ስለሆነ ነው።" አሉ።