+ -

عن شداد بن أوس رضي الله عنه قال: ثِنْتَانِ حَفِظْتُهُمَا عَنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ اللهَ كَتَبَ الْإِحْسَانَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ، فَإِذَا قَتَلْتُمْ فَأَحْسِنُوا الْقِتْلَةَ، وَإِذَا ذَبَحْتُمْ فَأَحْسِنُوا الذَّبْحَ، وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ، فَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1955]
المزيــد ...

ከሸዳድ ቢን አውስ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: ሁለቱን ከአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ንግግር ሸምድጃለሁ፦
"አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል። የገደላችሁ ጊዜ አገዳደላችሁን አሳምሩ፤ ያረዳችሁም ጊዜ አስተራረዳችሁን አሳምሩ። አንዳችሁ ቢላውን ይሞርድ እርዱንም ይገላግለው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1955]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ በኛ ላይ በሁሉም ነገሮችኢሕሳንን ግዴታ እንዳደረገ ተናገሩ። ማሳመር (ኢሕሳን) ማለት በአምልኮውም ውስጥ፣ መልካምን ሲፈፅምም፣ ከፍጡራን ላይ ጎጂን ነገር ሲያስወግድም ዘወትር አላህ ያየኛል ማለት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በመግደልና በማረድ ውስጥ ማሳመርም አንዱ ነው።
በመግደል ኢሕሳን ሲባል በቂሷስ (ሸሪዐዊ የቅጣት ብይን ለምሳሌ የገደለ መገደል) ተፈፃሚነት ወቅት: ለመግደል ገሩን፣ ቀላሉንና የተገዳዩን ነፍስ በፍጥነት ሊያወጣ የሚችለውን መንገድ በመምረጥ ነው።
በእርድ ማሳመር ሲባል ደግሞ እንስሳ በምናርድበት ወቅት ነው። ይህም መሳሪያውን በደንብ በመሞረድ ፣ የሚታረደው እንስሳ እያየ ፊት ለፊቱ ባለመሞረድና ሌላ እርዱን የሚመለከት እንስሳ ቦታው ላይ እያለ ባለማረድ ለእንስሳ በማዘን ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የላቀውና የተከበረው አላህ በፍጡራኑ ላይ ያለው እዝነትና ርህራሄን፤
  2. አገዳደልና አስተራረድ ላይ ኢሕሳን የሚባለው ሸሪዐውን የተከተለ (የዋጀ) በሆነ መልኩ ሲፈፀም ነው።
  3. ሸሪዐ ምሉዕና ሁሉንም መልካም ነገር የጠቀለለ ሲሆን ከዚህም መካከል ለእንስሳት ማዘኑና መራራቱ አንዱ ነው፤
  4. የሰውን ልጅ ከገደሉ በኋላ ሰውነቱን መቆራረጥ መከልከሉን፤
  5. እንስሳትን መቅጣት ያለበት ነገር ሁሉ ክልክል መሆኑን ተረድተናል።