عَنْ أَبِي مُوسَى رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ اللهَ عَزَّ وَجَلَّ يَبْسُطُ يَدَهُ بِاللَّيْلِ لِيَتُوبَ مُسِيءُ النَّهَارِ، وَيَبْسُطُ يَدَهُ بِالنَّهَارِ لِيَتُوبَ مُسِيءُ اللَّيْلِ، حَتَّى تَطْلُعَ الشَّمْسُ مِنْ مَغْرِبِهَا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2759]
المزيــد ...
ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ:
"አላህ ዐዘ ወጀል በቀን ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) በምሽት እጁን ይዘረጋል። በምሽት ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) ደግሞ በቀን እጁን ይዘረጋል። ይህም ፀሀይ በመግቢያዋ በኩል እስክትወጣ ድረስ ቀጣይ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2759]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ከባሮቹ ንስሀቸውን እንደሚቀበል ተናገሩ። አንድ ባሪያ በቀን ወንጀል ሰርቶ በምሽት ንስሀ ከገባም አላህ ንስሀውን ይቀበለዋል። በምሽት ወንጀል ሰርቶ በቀን ንስሀ ከገባም አላህ ንስሀውን ይቀበለዋል። አሏህ ንስሀ ለሚገቡ ሰዎች እጁን የሚዘረጋውም በንስሀቸው ስለሚደሰትና ንስሀቸውንም ለመቀበል ነው። የዚህ አለም ፍፃሜን የምታሳውቀው የፀሀይ ከመግቢያዋ በኩል መውጣት እስኪከሰት ድረስም የንስሀ በር ክፍት ከመሆን አይወገድም። ፀሀይ በመግቢያዋ በኩል የወጣች ጊዜ ግን የንስሀ በር ይዘጋል።