+ -

عَن الحَسَنِ قال: حَدَّثنا جُنْدَبُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ رضي الله عنه، فِي هَذَا المَسْجِدِ، وَمَا نَسِينَا مُنْذُ حَدَّثَنَا، وَمَا نَخْشَى أَنْ يَكُونَ جُنْدُبٌ كَذَبَ عَلَى رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلّى الله عليه وسلم:
«كَانَ فِيمَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ رَجُلٌ بِهِ جُرْحٌ، فَجَزِعَ، فَأَخَذَ سِكِّينًا فَحَزَّ بِهَا يَدَهُ، فَمَا رَقَأَ الدَّمُ حَتَّى مَاتَ، قَالَ اللَّهُ تَعَالَى: بَادَرَنِي عَبْدِي بِنَفْسِهِ، حَرَّمْتُ عَلَيْهِ الجَنَّةَ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3463]
المزيــد ...

ከሐሰን እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ጁንዱብ ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እዚሁ መስጂድ ውስጥ ነገሩን። ከነገሩን ጀምሮም አልረሳነውም። ጁንዱብም በአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ዋሽቷል ብለንም በፍፁም አንፈራም። እንዲህም አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ከናንተ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል አንድ የቆሰለ ሰውዬ ነበር። ትእግስት በማጣቱም ቢላ አንስቶ እጁን ቆረጠ። እስኪሞት ድረስም ደሙ አልተቋረጠም። አላህም እንዲህ አለ: 'ባሪያዬ ነፍሱን በማውጣት ተቻኮለኝ። በርሱ ላይም ጀነትን እርም አድርጌበታለሁ።' "

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3463]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከኛ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል መቁሰል ያጋጠመው አንድ ሰውዬ እንደነበር፤ በህመሙ ባለመታገስም ቢላ ይዞ እጁን በመቁረጥ ለመሞት እንደተቻኮለ፤ ደሙም እስኪሞት ድረስ አለመቋረጡን፤ አላህም "ባሪያዬ ነፍሱን በማውጣት ተቻኮለ። በርሱ ላይም ጀነትን እርም አድርጌበታለሁ።" ማለቱን ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በመከራ ላይ መታገስ ያለውን ደረጃና ከዛ የባሰ ወደሆነ መከራ እንዳያመራ ለሚያጋጥሙ ህመሞች ማማረርን መተው እንደሚገባ እንረዳለን።
  2. ስላለፉ ህዝቦች መልካምና ትምህርት የሚወሰድበትን ነገር ማውራት እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  3. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የአላህ ሐቆችን ሳይተላለፉ መቆም እንደሚገባ፤ ፍጡራንን ነፍሳቸውን ከማጥፋት በመከልከል ለነርሱ ያለውን እዝነትና ነፍሶችም የአላህ እንደሆኑ እንረዳለን።"
  4. ነፍስን ወደ ማጥፋት የሚያመሩ ሰበቦችን ከመጠቀም መከልከሉንና ነፍስን በማጥፋት ዙሪያ ከባድ ዛቻ መምጣቱን ተረድተናል።
  5. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ከሐዲሡ የምንረዳው እጁን የቆረጠው ሞትን በመፈለግ እንጂ ጥቅሙ አመዛኝ በሚሆን መልኩ ህክምናን አስቦ እንዳልነበረ ነው።"