عَنْ أَنَسٍ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ:
ضَحَّى النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِكَبْشَيْنِ أَمْلَحَيْنِ أَقْرَنَيْنِ، ذَبَحَهُمَا بِيَدِهِ، وَسَمَّى وَكَبَّرَ، وَوَضَعَ رِجْلَهُ عَلَى صِفَاحِهِمَا.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5565]
المزيــد ...
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:
«ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኡዱሒያ ሁለት ቡራቡሬና ቀንዳም የሆኑ ሙክቶችን በእጃቸው አረዱ። "ቢስሚላህ አላሁ አክበር" አሉና እግራቸውን አንገቱ ላይ አድርገው አረዱት።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5565]
አነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የዒድ አልአድሓ ቀን በእጃቸው ሁለት ቀንዳሞችና ጥቁር የተቀላቀለባቸው ነጫጭ ወንድ ሙክት በጎችን "ቢስሚላህ አላሁ አክበር" በማለት እግራቸውን አንገታቸው ላይ አድርገው እንዳረዱ ተናገረ።