عَن أُمِّ سَلَمَةَ أُمِّ المُؤْمِنينَ زَوْجِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ رضي الله عنها قَالت: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ كَانَ لَهُ ذِبْحٌ يَذْبَحُهُ فَإِذَا أُهِلَّ هِلَالُ ذِي الْحِجَّةِ، فَلَا يَأْخُذَنَّ مِنْ شَعْرِهِ، وَلَا مِنْ أَظْفَارِهِ شَيْئًا حَتَّى يُضَحِّيَ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1977]
المزيــد ...
የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሚስትና የአማኞች እናት ከሆነችው ከኡሙ ሰለማ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ:
"ለርሱ (ለኡዱሒያ) የሚታረድ እርድ ያለው ሰው የዙልሒጃ ጨረቃ የወጣች ጊዜ ኡዱሒያውን እስኪያርድ ድረስ ከፀጉሩም ይሁን ከጥፍሩ አንዳችም እንዳይቆርጥ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1977]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ኡዱሒያን ማረድ የፈለገ ሰው የዙልሒጃ ጨረቃ ግልፅ የሆነ ጊዜ ኡዱሒያውን እስኪያርድ ድረስ ከጭንቅላቱ ወይም ከብብቱ ወይም ከቀድሞ ቀመሱ ወይም ከሌላ አካሉ ላይ ያለን ፀጉርና የእጁን ወይም የእግሩን ጥፍርም እንዳይቆረጥ አዘዙ።