عَنْ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ سَمُرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَا تَحْلِفُوا بِالطَّوَاغِي، وَلَا بِآبَائِكُمْ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1648]
المزيــد ...
ከዐብዲረሕማን ቢን ሰሙራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"በጣዖታትም ሆነ በአባቶቻችሁ አትማሉ።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1648]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አጋርያኖች ከአላህ ውጪ ያመልኳቸው በነበሩትና ለክህደታቸውና ጥመታቸው ምክንያት በነበሩት ጣዖታት ከመማል ከለከሉ። በድንቁርና ዘመን የዐረቦች ልማድ ከነበሩት ነገሮች መካከል ለመኩራራትና ለማላቅ በአባቶቻቸው መማል ነበርና ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአባቶች ከመማልም ከለከሉ።