عَنْ أَبِي مُوسَى رضي الله عنه قَالَ:
سُئِلَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ الرَّجُلِ يُقَاتِلُ شَجَاعَةً، وَيُقَاتِلُ حَمِيَّةً، وَيُقَاتِلُ رِيَاءً، أَيُّ ذَلِكَ فِي سَبِيلِ اللهِ؟ فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «مَنْ قَاتَلَ لِتَكُونَ كَلِمَةُ اللهِ هِيَ الْعُلْيَا، فَهُوَ فِي سَبِيلِ اللهِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1904]
المزيــد ...
ከአቡ ሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጀግንነት ስለሚጋደል፣ ለወገንተኝነት ስለሚጋደልና ለይዩልኝ ስለሚጋደል ሰው ተነስቶ ‹በአላህ መንገድ የተጋደለው የትኛው ነው?› ተብለው ተጠየቁ። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን አስቦ የተዋጋ ሰው በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው እርሱ ነው።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1904]
ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተዋጊዎች አላማ ስለመለያየት ተጠየቁ። ለጀግንነት ወይም ለወገንተኝነት ወይም ደረጃው ሰው ዘንድ እንዲታይለት ወይም ከዚህ ውጪ ላለ አላማም ከተጋደለ ሰው መካከል በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው ማንኛው ነው? ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ የሚጋደል የሚባለው ሰው የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን የተጋደለ ሰው መሆኑን ተናገሩ።