+ -

عَنْ سَهْلِ بْنِ سَعْدٍ السَّاعِدِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«رِبَاطُ يَوْمٍ فِي سَبِيلِ اللَّهِ خَيْرٌ مِنَ الدُّنْيَا وَمَا عَلَيْهَا، وَمَوْضِعُ سَوْطِ أَحَدِكُمْ مِنَ الجَنَّةِ خَيْرٌ مِنَ الدُّنْيَا وَمَا عَلَيْهَا، وَالرَّوْحَةُ يَرُوحُهَا العَبْدُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَوِ الغَدْوَةُ خَيْرٌ مِنَ الدُّنْيَا وَمَا عَلَيْهَا».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2892]
المزيــد ...

ከሰህል ቢን ሰዕድ አስሳዒዲይ ረዲየላሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ለአንድ ቀን በአላህ መንገድ ኬላ መጠበቅ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል፤ አንዳችሁ ጀነት ውስጥ ያለው አለንጋ የሚያህል ቦታ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል፤ ባሪያው በአላህ መንገድ ማልዶ መጓዙ ወይም አርፍዶ መጓዙ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2892]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሙስሊሞችን ከከሃዲያን ለመጠበቅ ስራውን ለአላህ አጥርቶ በሙስሊሞችና በከሃዲዎች መካከል ያለ ኬላ ላይ ጥበቃ እያደረጉ አንድ ቀንም ማሳለፍ ከዱንያና ውስጧ ካለው እንደሚበልጥ፤ አንድ ባሪያ ጀነት ውስጥ በአላህ መንገድ የሚታገልበት አለንጋ ያህል ቦታ ማግኘቱ ከዱንያና ውስጧ ካለው እንደሚበልጥ፤ ከቀኑ መጀመሪያ እስከ ዝሁር ድረስ ባለው ወይም ከዝሁር ወቅት እስከ ምሽት ድረስ ባለው ጊዜ በአላህ መንገድ አንድ ጊዜ የመጓዝ ምንዳና አጅር ከዱንያና ውስጧ ካለው እንደሚበልጥ ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በአላህ መንገድ ኬላ መጠበቅ ያለውን ደረጃ እንረዳለን። ይህም ነፍስን አደጋ ውስጥ መክተት ስለሚጠይቅ፤ በርሱ አማካይነት የአላህ ንግግር ከፍ ስለሚልና የአላህን ሃይማኖት መርዳት ስለሆነ ነው። ስለዚህም የአንድ ቀኑ ምንዳ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል።
  2. ከመጪው አለም አንፃር ዱንያ የወረደች መሆኗን እንረዳለን። ምክንያቱም ጀነት ውስጥ የሚገኝ አለንጋ የሚያህል ስፍራ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣልና።
  3. በአላህ መንገድ የመታገልን ደረጃና የምንዳውን ትልቅነት እንረዳለን። ለጂሃድ ማልዶ ወይም አርፍዶ አንድ ጊዜ የመሄድ ምንዳ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣልና።
  4. ሐዲሡ ውስጥ "በአላህ መንገድ" ማለታቸው ስራን ለአላህ ማጥራት አንገብጋቢ መሆኑንና ምንዳም እርሱን ተከትሎ እንደሚሰጥ ይጠቁማል።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ