عن جابر بن عبد الله رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«كُلُّ مَعْرُوفٍ صَدَقَةٌ».

[صحيح] - [رواه البخاري من حديث جابر، ورواه مسلم من حديث حذيفة] - [صحيح البخاري: 6021]
المزيــد ...

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"መልካም ነገሮች ሁሉ ምፅዋት ናቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ከጃቢር በተላለፈ ሐዲሥ ሙስሊም ደግሞ ከሑዘይፋ በተላለፈ ሐዲሥ አውርተውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6021]

ትንታኔ

በንግግርም ይሁን በተግባር ለሌሎች የምንውለው በጎነትና ጥቅም ሁሉ ምፅዋት እንደሚሆንና በሱም ምንዳና አጅር እንደምናገኝበት ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ምፅዋት የሰው ልጅ ከገንዘቡ በሚያወጣው ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን የሰው ልጅ ወደ ሌሎች በሚደርስ መልኩ የሚሰራውና የሚናገረውን ሁሉ መልካም ነገሮችን ያቀፈ ነው።
  2. በዚህ ሀዲስ ውስጥ ለመልካምና ለሌሎች ጥቅም ላለው ነገር ሁሉ መልፋትን ያነሳሳል።
  3. ትንሽም እንኳን ብትሆን ከመልካም ነገር አንዳችም ማሳነስ እንደማይገባ እንረዳለን።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (67)