عن أنس بن مالك رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ أَحَبَّ أَنْ يُبْسَطَ لَهُ فِي رِزْقِهِ، وَيُنْسَأَ لَهُ فِي أَثَرِهِ، فَلْيَصِلْ رَحِمَهُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5986]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5986]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቅርብ ዘመዶችን በመዘየር ፣ በአካላዊና ገንዘባዊ ጉዳይ በማገዝና በሌሎችም መልኩ ዝምድናን በመቀጠል ላይ አነሳሱ። በተጨማሪም ዝምድናን መቀጠል ለሲሳይ መስፋትና ለእድሜ መርዘም ምክንያት መሆኑንም ተናገሩ።