عَنْ أَبِي الدَّرْدَاءِ رضي الله عنه أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَا شَيْءٌ أَثْقَلُ فِي مِيزَانِ الْمُؤْمِنِ يَوْمَ القِيَامَةِ مِنْ خُلُقٍ حَسَنٍ، وَإِنَّ اللَّهَ لَيُبْغِضُ الفَاحِشَ البَذِيءَ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي] - [سنن الترمذي: 2002]
المزيــد ...
ከአቡ ደርዳእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ:
"የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2002]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የትንሳኤ ቀን ከተግባሮችም ከንግግሮችም የአማኝን ሚዛን የሚደፋለት መልካም ስነ ምግባር መሆኑን ተናገሩ። ይህም ፊትን ፈታ በማድረግ፣ ሌላን ከመጉዳት በመቆጠብና መልካም ነገርን ለሌሎች በመለገስ ነው። የላቀው አላህ፤ በድርጊትም ይሁን በንግግር አፀያፊ የሆነንም በአንደበቱ ብልግና የሚናገርንም ሰው ይጠላል።