+ -

عَنِ ابْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لاَ يَنْظُرُ اللَّهُ إِلَى مَنْ جَرَّ ثَوْبَهُ خُيَلاَءَ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5783]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ለኩራት ልብሱን የጎተተን ሰው አላህ አይመለከተውም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5783]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በኩራትና በመደነቅ ልብስን ወይም ሽርጥን ከቁርጭምጭሚት በታች መልቀቅን አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመ ሰውም የትንሳኤ ቀን አላህ ወደርሱ በእዝነት እይታ እንደማያየው በመግለፅ ለከባድ ዛቻ የተገባ መሆኑን ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ልብስ ሲባል እንደሱሪ፣ ሽርጥና የመሳሰሉትን የታችኛውን የሰውነት ክፍል ሊሸፍን የሚችልን ሁሉ ይጠቀልላል።
  2. ልብስ በማርዘም ዙሪያ የመጣው ክልከላ ወንዶችን ብቻ ነው የሚመለከተው። ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ዑለማዎች ባጠቃላይ ለሴት ልጅ ማርዘም እንደሚፈቀድ ተስማምተዋል። ሴቶች የቀሚሳቸውን ጫፍ አንድ ስንዝር እንዲለቁ ከነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ፍቃድ መገኘቱ ተረጋግጧል።"
  3. ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል: "ልብስን ማርዘም የሐዲሦች ጥቅል ሀሳብ ስለሚጠቁም ክልክልና ሐራም ነው። ቅጣቶቹ ግን ይበላለጣሉ። የግድ እኩል መሆንም አይጠበቅባቸውም። ኩራትን አስቦ ያስረዘመ ሰው የሚቀጣው ቅጣት ሳያስብ እንዳስረዘመው አይደለም።"
  4. ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል: "ሴት ልጅ መላ አካሏ ሀፍረተ ገላ ነው። ስለዚህም ልብሷን አንድ ስንዝር ወደታች ብትለቅ ከልካይ የላትም። አንድ ስንዝር ራሱ ካልበቃት ከቁርጭምጭሚቷ ጀምራ አንድ ክንድ ወደ ታች ትለቃለች።"
  5. ቃዲ እንዲህ ብለዋል: «ዑለማዎች እንዲህ ብለዋል: "በጥቅሉ በልብስ ዙሪያ ከአስፈላጊውና ከተለመደው ርዝማኔም ይሁን ስፋት የጨመረ ሁሉ ይጠላል።" ይበልጡን አላህ ያውቃል።»
  6. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከጀለቢያና ከሽርጥ ጫፍ (ከጉልበት ስር) ወደ ታች ከሚወርደው ተወዳጁ መጠን የባት ግማሽ ድረስ ነው። ከባት ግማሽ እስከ ቁርጭምጭሚት መሃል ድረስ ቢያደርገውም ችግር የለውም። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ካለ ግን እርሱ እሳት ውስጥ ነው። ተወዳጁ የባት ግማሽ ድረስ ሲሆን ሳይጠላ የሚፈቀደው ደግሞ ከባት ግማሽ በታች እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ ነው። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ያለው ደግሞ የተከለከለው ነው።"
  7. ኢብኑ ዑሠይሚን (አላህ ወደርሱ አይመለከትም።) በሚለው ዙሪያ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ማለት የእዝነትና የርህራሄ እይታ አያየውም ማለት ነው እንጂ በጥቅሉ አያየውም ማለት አይደለም። ምክንያቱም አላህ በርሱ ላይ አንዳችም አይደበቅበትም፤ አንዳችም ነገር ከእይታው አይሰወርበትምም። ነገር ግን ከሐዲሡ የተፈለገው የእዝነትና የርህራሄ እይታ ነው።"