عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«لَا تَجْعَلُوا بُيُوتَكُمْ قُبُورًا، وَلَا تَجْعَلُوا قَبْرِي عِيدًا، وَصَلُّوا عَلَيَّ؛ فَإِنَّ صَلَاتَكُمْ تَبْلُغُنِي حَيْثُ كُنْتُمْ».
[حسن] - [رواه أبو داود] - [سنن أبي داود: 2042]
المزيــد ...
አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል: የአሏህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡
"ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ! ቀብሬንም የሚጎበኝ የበአል ስፍራ አታድርጉት! ይልቅ በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ! የትም ብትሆኑ ሶለዋታችሁ ትደርሰኛለችና።"
[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 2042]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤቶችን እንደ መቃብር ከሶላት የተገለሉ እና ሶላት የማይሰገድባቸው ከማድረግ እየከለከሉ ነው። እንዲሁም ልማድ አድርጎ በመያዝ የሳቸውን ቀብር ደጋግሞ መጎብኘቱንም እዚያው መሰብሰቡም ወደ ሽርክ ስለሚያደርስ ከለከሉ። ከዛ ይልቅ ወደ ቀብራቸው መመላለስ ሳያስፈልግ ቅርብም ይሁን ሩቅ እኩል ለእርሳቸው ስለሚደርሳቸው ከየትኛውም ቦታ ሆነን በሳቸው ላይ ሶለዋት እንድናወርድ አዘዙን።